Home ዜና የትግራይ ህዝብ ፀረ ባርነት የነፃነት ተጋድሎ በትውልድ ቅብብሎሽ እየቀጠለ መሆኑ የትግራይ ሴ/...

የትግራይ ህዝብ ፀረ ባርነት የነፃነት ተጋድሎ በትውልድ ቅብብሎሽ እየቀጠለ መሆኑ የትግራይ ሴ/  ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው

553
0

የትግራይ ህዝብ ፀረ ባርነት የነፃነት ተጋድሎ በትውልድ ቅብብሎሽ እየቀጠለ መሆኑ የትግራይ ሴ/  ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ተናገሩ ፡፡

—–

የዛሬ ዓመት በያዝነው ሳምንት የተጀመረው ዘመቻ አሉላ አባነጋ የትግራይ ህዝብ አይበገሬነት የፀረ ጭቆና እና ፀረ ባርነት የነፃነት ተጋድሎ በትውልድ ቅብብሎሽ እየቀጠለ መሆኑ በተግባር የተረጋገጠበት ታሪካዊ ዘመቻ ነው ሲሉ የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።

አክለውም ዘንድሮ የሚከበረው የትግራይ ሰማእታት ቀን አዲስ ሰማእታት  ያስተናገድንበት ሆኗል ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ የትላንትም የዛሬም ሰማእታት አደራ በመቀበል የትግራይ ህዝብ ራስን በራስ ለማስተዳደር የሚያደርገው እንቅስቃሴ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ የትግራይ ህዝብ፤ የትግራይ ሰራዊት እና መንግስት ወትሮም ዝግጁ መሆናቸው አረጋግጧል።

እንደ ዱቄት ተበትንኗል ሲባል የነበረው የትግራይ ሰራዊት በዘመቻ አሉላ አባነጋ ጠላት ሲመካበት የነበረውን ሁሉን አቅሙ በቀናት ውስጥ በማፈራረስ  የትግራይ ህዝብ ህጋዊ መንግስቱ ወደ መንበሩ እንዲመለስ ያስቻለ በቆላ ተምቤን ከተመዘገቡ ድሎች በላይ ትርጉም ያላቸው ድሎች የተመዘገቡበት ዘመቻ ነበር ሲሉ የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።

በዘመቻ አሉላ አባነጋ በአጭር ጊዜ ስልጠና ወስዶ የጠላትን ሃይል እንዳልነበረ አድርጎ የደመሰሰው የትግራይ ሰራዊት በአሁን ወቅት የትግራይን ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለማረጋገጥ  በዘመቻ አሉላ አባነጋ የተመዘገቡ ድሎችን በብዙ እጥፍ መድገም የሚችል በተሻለ አደረጃጀት አቅምና ቁመና የሚገኝ ሰራዊት ስለመሆኑም ነው የሚገልፁት።

ዘንድሮ ለ34ኛ ግዜ እየተከበረ ያለው የትግራይ ሰማእታት ቀን አዲስ ሰማእታት ያስተናገድንበት ሆኗል ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ  የትላንትም  የዛሬም ሰማእታት አደራ በመቀበል የትግራይ ህዝብ ራስን በራስ ለማስተዳደር የሚያደርገው እንቅስቃሴ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ የትግራይ ህዝብ፤ የትግራይ ሰራዊት እና መንግስት ዝግጁ መሆናቸው አረጋግጣዋል።

በተጨማሪምየትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ጥቅሞች እና ፍላጎቶች ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ የሚቻልበት የሰላም እድል እስከተፈጠረ ድረስ የትግራይ መንግስት ሁሌም ለሰላም ቁርጠኛ መሆኑን የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ።

የትግራይ ህዝብ ህልውና ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ ተስፋፊው የአማራ ሃይል እና አምባገነኑ ኢሳያስ አፍወርቂ አሁንም ቢሆን የሰላም ጭላንጭል ለማኮላሸት እና የትግራይ ህዝብን ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት ለሚፈፁሙት ትንኮሳዎች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ ተጣድፈን ወደ ግጭት ላለመግባት እየጣርን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳይ አስመልክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የትግራይ መንግስት ሁሌም ለሰላም ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ እየተካሄዱ ያሉ የሰላም ጥረቶች በሚመለከት መንግስታቸው የያዘውን አቋም አብራርተዋል።

የሰላም ሂደቱ ለማስጀመር በምን ጉዳይ እና ምን አጀንዳ  ይዘን እንወያይ የሚለውን  ለማየት የሚያስችል  የመጀመርያ ደረጃ ውይይት ለማድረግ የሚያስችል ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ በፋሽስቱ ቡድን በኩል ከፍላጎት በዘለለ በተግባር ሊፈፀም ይገባል ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ፍላጎቶች እና ጥቅሞች በሰላም የሚፈቱ ከሆነ ለሰላም ዝግጁ  ነን ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ ካልሆነ ግን  የህዝቡን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እስኪረጋገጥ ድረስ ሁሉንም ዓይነት  አማራጮች እንጠቀማለን ሲሉም አስምረውበታል።

ተሰፋፊው የአማራ ሃይል እና አምባገነኑ ኢሳያስ አፍወርቂ የታየውን የሰላም ጭላንጭል  ለማደናቀፍና የትግራይ ህዝብን ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት ትንኮሳዎች አሁንም ቀጥለዋል ብለዋል አቶ ጌታቸው ረዳ። ለነዚህ ትንኮሳዎች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ ተጣድፈን ወደ ግጭት ላለመግባት እየጣርን ነው ሲልም አክለዋል።

Previous articleረሃብን እንደጦር መሳርያ በመጠቀም በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመ መሆኑ The conversation ድረገፅ አስነበበ፡፡
Next articleሩሲያና ቻይና ፋሽስቱ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጠረውን የረሃብ ቸነፈር አፋጣኝ መፍትሄ እንዳያገኝ ማደናቀፋቸው ማርክ ሎውኮክ ገለፁ፡፡