Home ዜና የትግራይ መንግስት  ማእከላዊ ኮማንድ መግለጫ

የትግራይ መንግስት  ማእከላዊ ኮማንድ መግለጫ

2416
0

ፈተናዎችን ተሻግሮ  ህዝባዊ ትግላችን  ያሸንፋል//

ጥምር ወራሪ ሃይሎች የትግራይ ህዝብ  ለአንዴና ለመጨረሻ ከምድረገፅ ለማጥፋት በሁሉም ግንባሮች መጠነ ሰፊ ወረራዎች እያካሄዱ ሲሆን የትግራይ ሰራዊት  በበኩሉ የህዝቡን ህልውና   ለማስጠበቅ ሲል  በአስገራሚ ፅናት፣ ታሪካዊው ተጋድሎ እያካሄደ ይገኛል፡፡   ደመኞቹ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች በረገጡት አከባቢዎች ህዝባችን በጅምላ በመጨፍጨፍ እየፈፀሙት ያለው ጀኖሳይድ በከፋ መልኩ ቀጥሎውበታል ፡፡

እነዚህ የጥፋት ሃይሎች በሁሉም አቅጣጫ የጀመሩት ግልፅ  ወረራ አጠናክረው እየቀጠሉ በት ሲሆን ትናንት ጥቅምት 7 2015   ዓ/ም ወደ ሽረ እንዳስላሰ ከተማ ገብተዋል፡፡ ጀግናው የትግራይ ሰራዊትም    የሞት የሽረት ትግሉን በላቀ ጀግንነት እያካሄደ  ነው፡፡

በማንኛውም ውግያ የቦታ መገፋፋት ተፈጥሮአዊና ያለ ሲሆን   ወራሪ  ሃይሎቹ የሽረ ከተማን ጨምሮ  አንድ አንድ አከባቢዎች ለጊዜው ቢቆጣጠሩም የመጨረሻው ድል የትግራይ ህዝብ መሆኑ በመረዳት እያንዳንዱ ትግራዋይ አቅሙ በፈቀደውን  በፅናት ሊመክተው ይገባል፡፡ ጠላቶቻችን  ሙሉ አቅማችን ተጠቅመን ካልመከትናቸው  እስከ አሁን  ሲፈፅሙት የቆዩትን   ግፍና በደል በከፋ ደረጃ  በዓለም ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ  ጭፍጨፋ  በኛ ላይ እንደሚፈፅሙ በመገንዘብ ሁሉም የትግራይ ህዝብ ሁለንተናዊ ትግሉን እንዲያጠናክር  ማእከላዊ  ኮማንዱ ጥሪ ያቀርባል፡፡

ጠላቶቻቸን እስከ አሁን በደረሱበት አከባቢ ባካሄዱት የመድፍ ድብደባዎች    በርካታ ሰላማውያን ዜጎች ለሞትና ጉዳት ሲዳረጉ በመቶ  ሺዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ ከጥይት አና ከበሽታ   የተረፈውን   የትግራይ ህዝብ ከቄዬው እያፈናቀሉ በረሃብ እንዲረግፍ ሁሉም አይነት ጥፋት እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡

የዓለም ማህበረ-ሰብ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ባለው ሁለንተናዊ በደልና የዓለም-አቀፍ ህጎች  ጥሰት በሚገባ ተረድቶ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጥና ግዴታው ሊወጣ ይገባል፡፡  

ስለሆነም ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም   የሰብአዊ እርዳታ ያለምንም መደናቀፍ ወደ ትግራይ እንዲገባ የአለም አቀፉ ማህበረ-ሰብ ሃላፊነቱን በአስቸኳይ እንዲወጣ ሲል የትግራይ ማእከላይ ኮማንድ ጥሪ ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም ጥምር ወራሪ ሃይሎች  የትግራይን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ  ለማጥፋት ያለ የሌለ አቅማቸውን አሟጠው እየተረባረቡ ቢሆኑም  የትግራይ ህዝብ ህልውናውን ለማረጋገጥ ሲል ቀና አላማ ይዞ ፍትሃዊ ትግሉን በፅናት እያካሄደ ያለ ህዝብ በመሆኑ  ሁሉም ፈተናዎች  መክቶ ድል እንደሚቀዳጅ አያጠራጥርም ፡፡

ስለሆነም በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ሁሉም ትግራዋይ ለማይቀረው ድል በሙሉ አቅሙ በመክተት  ታሪካዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ማእከላይ ኮማንድ ዳግም ጥሪ ያቀርባል፡፡

ህልውናችንና ደህንነታችን በክንዳችን ትግራይ ትስዕር//

የትግራይ መንግስት  ማእከላዊ ኮማንድ

 ጥቅምት7 2015 ዓ/ም

 መቐለ

Previous articleፕሮፌሰር ቶኒ ማጋና በዶ/ር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ በጤና አጠበበቅ ዘርፍ ስኬት ሪፖርት እጅግ ቅር መሰኘታቸውን ገለጹ::
Next article“የምዕራባውያን የዲፕሎማሲ ውድቀት በትግራይ ጦርነት“ ማርቲን ፕላውት