Home ዜና የትግራይ መንግስት ከ4200 በላይ ምርኮኞች ወደ የመጡበት አከባቢ እንዲመለሱ በምሕረት እንዲለቀቁ ወሰነ፡፡

የትግራይ መንግስት ከ4200 በላይ ምርኮኞች ወደ የመጡበት አከባቢ እንዲመለሱ በምሕረት እንዲለቀቁ ወሰነ፡፡

1984
0

ምህረት የተደረገላቸው ምርኮኞችም ወደ መጡበት አካባቢ ሲመለሱ በትግራይ ህዝብ የተፈፀመ ጀኖሳይድ ምስክር በመሆን ሌሎችን ለማስተማር የትግራይ ህዝብ የሰላም አምባሳደር ሆነው ጦርነትን ለማስቀረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

የትግራይ ህዝብና መንግስት ህልውናውን ለማረጋገጥ ሲል ተገዶ ወደ ጦርነት እንደገባ   ይታወቃል፡፡

ጀግናው የትግራይ ሰራዊት የትግራይ ህዝብን ህልውናውና ደህንነቱን ለማረጋገጥ ባደረገው  ትግልም ጠላቶች በመደምሰስና ድባቅ በመምታት አንጸባረቂ ድሎች እያስመዘገበ የሚማረኩ እየማረከ ሰሜን ሽዋ እንደደረሰና ለሰላም ብሎ ወደ ቦታው መመለሱን የቅርብ ትውስታችን ነው፡፡

የፋሽሽሰቱ ቡድን በሃሰት ፕሮፖጋንዳ ወጣቶች እያታለለ ወደ ጦርነት  መማጋዱን ሳያንስ ምንም እንኳ የተማረከ ሰራዊት የለኝም፣ አላውቃቸውም ፎቶ ሾፕ ነው ቢልም እውነቱ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ምርኮኛ ቅጥረኛ ሰራዊት በትግራይ የምርኮኞች ማእከል ይገኛሉ፡፡

አሁን ደግሞ 4 ሺህ 208 ምርኮኞች በምህረት እንዲለቀቁ የትግራይ መንግስት መወሰኑን በትግራይ የምርኮኞች ማእከል አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ከበደ ተናግረዋል፡፡

አቶ ብርሃኑ አክለውም ይህ የትግራይ መንግስት ውሳኔ የትግራይ ህዝብ መንግስትና ሰራዊቱ ከትግራዋይነት የሚመነጨው ለሰው ክብር መስጠት እና ሰብአዊነትን ማስቀደም የሚቀዳ መልካም እሴት ሲሆን የጀግንነት እና የአሸናፊነት መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

በምርኮኞች የሽኝት ፕሮግራም ላይ የተገኙ የሃይማኖት አባቶች የተለያዩ የህብረተ-ሰብ ክፍል ተወካዮች በትግራይ ህዝብ አስከፊ በደል እንደደረሰ በመግለጽ ያ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰው በደልና መከራ የኢትዮጰያ ህዝብ እንዲያውቀው ምርኮኞቹ የሰላም አምባሳደር ሆነው እንዲሰሩም መክረዋል ፡፡

ምህረት የተደረገላቸው ምርኮኞች በበኩላቸው በትግራይ በቆዩባቸው ጊዚያት  ለተደረገላቸው እንክብካቤ አመስግነዋል፡፡

ወልደሚካኤል ገ/መድህን

Previous articleየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠታቸው ተገለፀ።
Next articleበጀግናው የትግራይ ሰራዊት በጦር ግንባር የተማረኩ ከ4200  በላይ የፋሽስቱ አብይ ቡድን የጦር ምርኮኞች በምህረት ወደ ቀያቸው ተሸኙ።