Home ዜና የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ከፋሽስቱ ቡድን ጋር እስካሁን የተካሄደ...

የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ከፋሽስቱ ቡድን ጋር እስካሁን የተካሄደ ድርድር እንደሌለ ተናገሩ፡፡

1214
0

የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከፋሽስቱ ቡድን ጋር እስካሁን የተካሄደ ውይይት እንደሌለ እና የሰላም ሂደቱ አሁንም ቀደም ሲል በተደረሰው ግዚያዊ ግጭትን የማቆም ውሳኔ ላይ እንደሆነ አስታወቁ።

አክለውም የትግራይ መንግስት ለድርድር አይቀረቡም ብሎ ባስቀመጣቸው ዓበይት ነጥቦች ላይ አሁንም እንደማይደራደር ግልፅ አድርገዋል።

የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ የሰላም ሂደቱ ቀደም ሲል በተደረሰው ግዚያዊ ግጭትን የማቆም ውሳኔ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

የትግራይ መንግስት አሁንም ለሰላም ያለው  ቁርጠኝነትና አቋም የፀና እንደሆነ የገለፁት ዶክተር ደብረፅዮን እስካሁን የተካሄደ ውይይት ግን  እንደሌለ ተናግረዋል፤ የትግራይ ህዝብ የማያቀው በድብቅ የሚካሄድ ድርድር እንደማይኖር ግልፅ ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ  ውይይት ለማድረግም ቢሆን የሰብአዊ እርዳታው  እና የህዝባዊ አገልግሎቶች መክፈት በቅድሚያ ተፈፃሚ መሆን  ያለባቸው ጉዳዮች ስለመሆናቸው ሊዘነጉ እንደማይገባም  አክለዋል ።

የትግራይ መንግስት ለድርድር አይቀርቡም በማለት ያስቀመጣቸው የትግራይ ሰራዊት ጉዳይ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት፣ የትግራይ ህዝብ የሪፈረንደም፣ እንዲሁም የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት ከትግራይ  ምድር ተጠራርጎ የመውጣት እና በትግራይ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ የፈፀሙ እና እየፈፀሙ ያሉ አካላት ተጠያቂ የማድረግ ጉዳይ  አሁንም በፍፁም ወደ ድርድር እንደማይቀረቡ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስምረውበታል።

ስለሆነም በቅርቡ አንዳንድ ሚድያዎች ያሰራጩት የውሽት ወሬ ሆነ ተብሎ የተሰራጨ ስለመሆኑንም ነው ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ያብራሩት።

ታሪክ ፍስሃ

Previous articleበትግራይ ህዝብ ላይ በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ርሃብ ምክንያት አንዲት የአርባ ቀናት እድሜ ያለውን ህፃን እናት ህይወትዋ ማለፉ ተገለፀ፡፡
Next articleፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል(ዶክተር) በላኩት ደብዳቤ በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ ካለው ችግር አንጻር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል፡፡