Home ዜና የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበር ከትግራይ ህዝብ ጎን በመቆም ታሪክ የማይረሳው ድልመስራቱ የትግራይ...

የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበር ከትግራይ ህዝብ ጎን በመቆም ታሪክ የማይረሳው ድልመስራቱ የትግራይ መንግስት ገለፀ፡፡

982
0

የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አለም አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበር ከትግራይ ህዝብ ጎን በመቆም ታሪክ የማይረሳው ድል ማስመዝገባቸውን ገለጹ፡፡ 

በቀጣይም ትግራይ አሁን ከገጠማት ችግር እንድትወጣ ትግላቸውን አጠናክሮ እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አለም አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበር በበኩሉ የትግራይን ህዝብ ፍላጎት መሰረት በማድረግ  በትግራይ  ዘላቂ ሰላምና ደህንነት እንዲኖረው በትኩረት እስራለሁ ብሏል፡፡

አለም አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበር ትግራይ አሁን ካጋጠማት ችግር እንዴት መውጣት እንዳለባትና ትግራይን መልሶ ለመገንባት ምን መሰራት አለበት በሚል ዙሪያ በመቐለ በተደረገው የውይይት መድርክ የተገኙት የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ማህበሩ ከትግራይ ህዝብ ጎን በመቆም ታሪክ የማይረሳው ድል አስመዝግቧል ብለዋል፡፡

ማህበሩ ትግራይ ላይ የተፈፀመው ወረራ በመመከት ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል በተለይም የዲፕሎማሲ ስራዎችን በመስራት ጉልህ ሚና ነበረው ያሉት ዶክተር ደብረፅዮን በቀጣይም ትግራይ አሁን ከገጠማት ችግር እንድትወጣ ትግላቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

 የአለም አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ የትግራይ ህዝብን ፍላጎት መሰረት በማድረግ  የትግራይን ህዝብ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት እንዲኖረው ለማድረግ በምርምርና በፈጠራ የተጋዘ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ማህበሩ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሱትን የጀኖሳይድ ወንጀሎች እና ውድመቶች በማጥናት አለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲያውቃቸው ከማድረግ ባሻገር ትግራይን መልሶ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ምሁራን፣ ከፍተኛ የመንግስት ኋላፊዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን፤ የትግራይን ህዝብ አሁን ካጋጠመው የህልውና አደጋ እንዴት መውጣት እንዳለበትና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡   

ይብራህ እምባየ  

Previous articleበዓለማችን በሚገኙ 20 ሃገራት ውስጥ እጅግ የከፋ ረሃብ ሊከሰትባቸው እንደሚችል የዓለም OCHA እና WFP አስጠነቀቁ፡፡
Next articleየፋሽስቱ ቡድን  በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሰማራቸው ቅጥረኛ ሰራዊት በንፁሃን ዜጎች ላይ እየፈፀሙት ያለውን ግድያ፣ እንግልት፣ ቤት ንብረት ማቃጠልና ማውደም ከምንግዜም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡