Home ዜና የትግራይ ሰራዊት ከተሰጣቸው ህዝባዊ ሓላፊነት በተጨማሪ በልማት ስራዎች ላይ እያካሄዱት ያለው የልማት...

የትግራይ ሰራዊት ከተሰጣቸው ህዝባዊ ሓላፊነት በተጨማሪ በልማት ስራዎች ላይ እያካሄዱት ያለው የልማት ተሳትፎ ተጠናከሮ ቀጥለዋል፡፡

1122
0

የፋሽስቱ ብድን እና ግብረ አበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ባካሄዱት የጀኖሳይድ ጦርነት የወድሙ የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና አከባቢዎች መልሶ እንዲያገግም ለማድረግ የትግራይ ሰራዊት አመራሮችና አባላት በደቡብ ትግራይ ዞን በእንዳመኮኒ ወረዳ የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡

ለረዥም አመታት በጦርነት እና በድርቅ የተራቆተው አብዛኛው የትግራይ መሬት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና የዳግመ ግረባ ስራ በመስራት እና  ተራቁተው የነበሩ አካባቢዎች መልሶ  በማዳን አረንጋዴ አከባቢዎችን በመፍጠር ትግራይ በአለም አቀፍ ደረጃ  እውቅና የተሰጣት እንደነበረች የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በትግራይ ህዝብ ላይ ተኝተው የማያድሩት ጠላቶች ባወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት ከፍተኛ ውድመት አድርሰዋል በዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘውን የትግራይ ተፈጥሮ ሃብት ስራ ወደ ኃላ መልሰውታል

ለህልውናው እና ለህዝባቸው ሲሉ እየተዋደቁ ያሉት የጀግናው የትግራይ ሰራዊት አመራር አባለት ታዲያ በዚህ ክረምት የተራቆተውን የትግራይ አካባቢ ዳግም እንዲያገግም በደቡብ ትግራይ ዞን እንዳሞኮኒ ወረዳና አካባቢዋ በመገኘት የችግኝ ተከላ ስራ አከናውነዋል፡፡

የሰራዊቱ አባላት በበኩላቸው የተጠሳቸውን የህዝባቸው ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ህዝባዊ ሓላፊነት በተጨማሪ ከማህበረሳባቸው ጋር በልማት ስራዎች ላይ ተባብረው እያለሙ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

የእንዳሞኮኒ ወረዳ አስተዳዳሪ ኣቶ ሃፍቱ በርሀ የትግራይ ሰራዊት አባላት ከተሰጣቸው ህዝባዊ ሓላፊነት በተጨማሪ በልማት ስራዎች ላይ እያካሄዱት ያለው የልማት ተሳትፎ የሚደነቅና ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

ሄለን ሃፍቱ 

Previous articleለከፋ ረሃብና ችግር የተጋለጠውን የዋግ-ኽምራ ቢርቢጣ ወረዳ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብለት ጥሪ ቀረበ።
Next articleየትግራይ ተወላጅ አትሌቶች ድልና ደስታ ከቤተሰብ ጋር መጋራት አለመቻል