Home ዜና የትግራይ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከፍተኛ ቤተ ክህነት መንበረ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን የሊቃነ...

የትግራይ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከፍተኛ ቤተ ክህነት መንበረ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን የሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ።

1328
0

የትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ ለመላው ዓለም ሰላምን በመመኘት በተለይም ሃገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ ስለምትገኝ መላው ህዝባችን ሁሌም ስለ ሰላም ሊፀልይና ሁሉም መሪዎች ስለ ሰላም ሊያስቡና ሊወያዩ፣ በምግብና በመድሃኒት እየሞተ ያለው ህዝባችን ያለ ማቋረጥ እርዳታ እንዲገባ፣ ስልክ፣ ባንክ፣ ኢንተርኔት፣ መብራት እና የትራንስፖርት አገልግሎት በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል። 

የትግራይ ህዝብ በመጪው የክረምት ወራት ተክሎችን እንዲተከል፣ የተተከሉትም እንዲንከባከብ አርሶ አደሩም የተሻለ ምርት እንዲያገኝ ሌትና ቀን መስራት እንዳለበት የትግራይ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከፍተኛ ቤተ ክህነት መንበረ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን የሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ ጥሪውን አቅርቧል። 

በጉባኤው የትግራይ ኦርቶዶክስ ከፍተኛ ቤተ ክህነት መንበር ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የሚመሩ ግዚያዊ ስራ አስፈፃሚዎች የሹመት ደብዳቤ የተሰጠ ሲሆን  ለፅህፈት ቤቱ አገልግሎት የሚውል በጀትም ተወያይቶ ወስኗል።

በሃገር ውስጥና በውጭ የሚኖር መላው ህዝባችን ለትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ከፍተኛ ቤተ ክህነት መንበረ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን በሞራል በሃሳብና በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግም በጉባኤው ጥሪ ቀርቧል።

Previous articleብቸኛ የዜማ  ፈላስፋው የቅዱስ ያሬድ ልደትን የሚዘክር ልሳነ ግዕዝ ቅዱስ ያሬድ የጉባኤ መድረክ በአክሱም ከተማ ተካሂዷል፡፡
Next articleየአፍሪካውያን የሰላም ተምሳሌት ሆና ለሶስት አስርት ዓመታት የዘለቀችው ኢትዮጵያ  አሁን ላይ የኢሳያስ  መፈንጫ መሆኗተነገረ፡፡