Home ዜና የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረ-ሰብ በአሜሪካ አትላንታ ጆርጅያ ትግል

የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረ-ሰብ በአሜሪካ አትላንታ ጆርጅያ ትግል

1103
0

በአሜሪካ አትላንታ ጆርጅያ የሚኖሩ የትግራይ ዳያሰፖራ ማህበረ-ሰብ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የጀኖሳይድ ወንጀል ለግዛቲቱ ሴናተሮች አስረዱ፡፡
በማንኛውም የአለማችን ማእዝን የሚገኙ የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረ-ሰብ ከዓለም ተነጥሎ እንደ ዘር እንዲጠፋ የተፈረደበት የትግራይን ህዝብ ድምፅ በመሆን ባገኙት አጋጣሚ በመጠቀም ትግራይን በዓለም የተለያዩ መድረኮችን ከማስተዋወቅ ጀምሮ የትግራይ ጀኖሳይድ ፈፃሚዎች ገመናን በኣለም አደባባይ በማጋለጥ ታሪክ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
የትግራይ ህዝብ ሰቆቃ በእምባ አጅብው ለአለም አቀፍ ሚድያዎች እና ተቋማት ዝግ የሆነችው ትግራይን እያስተዋወቁ ይገኛሉ፡፡ በአዳራሹ የተሰበሰቡ ሴናተሮች እና እንግዶችም በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይና ሰቆቃ በሚገባ የተረዱት ይመስላል፡፡
ትግራይን ምድረ ገሀነም ያስመሰላት በሁለንተናዊ ከበባ ስር በማቆየትና እና ክልከላ በማድረግ ከ500 በላይ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ ሀገሬ በሚላት የፋሽስቱ ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊት፣ የተስፋፊ የአማራ ሀይልና በአምባገነኑ የኢሳያስ አራዊት ሰራዊት የሌሎች ሀገራት ቴክኖሎጂ ድጋፍ ታክሎበት ከአንድ አመት በላይ መጨፍጨፍ አሁንም ከጠላት ስር ባልወጡ የትግራይ ግዛቶች ውሰጥ ይህንኑ አረመኔያዊ ድርጊት መቀጠሉ በትግራይ እንስቶች የደረሰው ለመናገርም የሚሰቀጥጥ ዘግናኝ ፃታዊና ወሲባዊ ጥቃት ለአትላንታ ጆርጂያ ሴናተሮች እና ለዓለም ማህበረ-ሰብ አሳወቀዋል፡፡
የታፈነውን የትግራይን ህዝብ ድምፅ ያሰሙት የትግራይ ዳያስፖራ ማህበረ-ሰብ የጆርጆያ አትላንታ ነዋሪዎች በ2022 ኢትዮጵያ ለትግራይ ተወላጆች ታላቋ እስር ቤት ሆናለች፡፡ አለም ስለ ሴቶች መብት እና እኵልነት አብዝቼ እየሰራሁበት ነው በምትልበት ዘመን በ100 ሺዎቸ የሚቆጠሩ የትግራይ እኗቶች እና ህፃናት ግን በጅምላ ተደፍረዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ከ500 ቀናት በላይ ይቅርና ተመጣጣኝ ምግብ ሊያገኝ የሚላስ የሚቀመስ እጥቶ እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው ሲሉም ልብ በሚነካ አቀራረብ አቅርበዋል፡፡

የአለም ማህብረ-ሰብ ትግራይን አንድ አንድ የአለም ማህበረ-ሰብ አካል ከጎኑ ከመቆም ባሻገር ይህንን ህዝብ እንዲታድግ የዳያስፖራዎቹ ጥሪ ሲሆን ዓለም ይህንን ፍፁም እንዳይደገም ብላ የተማማለችለትን የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል የሆነውን የጀኖሳይድ ጦርነት በትግራይ ያዉም በ21 ኛው ክ/ዘመን ሲደገም ከተለመደው የአሳስቦናል ከሚል መግለጫ የዘለለ እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ አሁን እና አሁንነው የሚል ነው፤ በማለት በአሜሪካ ግዛት ውስጥ በጆርጀያ አትላንታ የሚገኙ የትግራይ ማህበረ-ሰብ ባሰሙት ድምፅ ከሴኔተሮችም በጎ ምላሽ አግኝተዋል፡፡

Previous articleየመብት ጥሰቶችን በገልተኝነት ለማጣራት ለተሰየመው ቡድን የኢትዮጵያ መንግስት በጀት አልፈቅድም ማለቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወቀሰ።
Next articleበትግራይክልል እርዳታ ማድረስ የተገደበ መሆኑን አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ፡፡