Home Uncategorized የአማራ ሊሂቃን የራሳቸውን ጥቅም እና የስልጣን ፍላጎት ለማሳካት ሲሉ ጭቁኑን የአማራ ህዝብ ...

የአማራ ሊሂቃን የራሳቸውን ጥቅም እና የስልጣን ፍላጎት ለማሳካት ሲሉ ጭቁኑን የአማራ ህዝብ  ከተለያዩ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር እያጋጩት መሆኑን ምሁራን ገለፁ፡፡

955
0

እነዚህ የትምህክት ሃይሎች በውሸት ትርክት የአማራ ህዝብ ብዙ ጠላት እንዳላው በማስመሰል ህዝቡ የሚያነሳውን ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው  የህልም እንጀራ እንደጠብቅ የፈጠሩት ሴራ መሆኑን የህግ ባለሞያዎቹ ገልፀዋል፡፡

የአማራ ተስፋፊ ሀይሎችና የአማራ ሊሂቃን የሌላን ዘር እያንቋሸሹ አንዱ የበላይ ሌላው የበታችነት እንዲሰማው ከማድረግ አልፈው  የአማራ ጭቁን ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጰያ ህዝቦች የተለየ ታሪክና ማንነት እንዳለው ይሰብካሉ፡፡

ይህም ሳያንሳቸው በፈጠሩት የውሸት ትርክትም የአማራ ህዝብ የግዛት ወሰን የለውም የተለየ ፍጡር ነህ እያሉ የግዛት ማስፋፋት ህልማቸውን ለማሳካት ሲሉ ህዝቡ ወደ  ለየለት እልቂት እንዲገባ ቀን ከሌት እየሰሩ መሆናቸው በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸወነ የሰጡን የህግ ምሁራን ይገልፃሉ፡፡

ይህን ተከትሎም እነዚህ ሊህቃን በሚያሰራጩት የጥላቻ መልእክት የአማራ ማህበረሰብን ከሌሎች የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ጋር እያጋጩት በመሆናቸው የሁሉም ጭቁን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የራሱ የአማራ ህዝብ ጠላት መሆናቸውን የህግ ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግፍና በደል በመፈፀም ላይ ያሉት የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች እና ሊሂቃን  የሚያደርጉት ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጭ የጥላቻ ንግግራቸው ሆነ ሰውን በአረሜኒያዊ መንገድ የመግደልና የመጨፍጨፍ ተግባራቸው በእርግጥም በጥላቻ የታወሩ ትምክህተኞች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን የህግ ባለሞያዎቹ ገልፀዋል፡፡

የህግ ባለሞያዎቹ አክለዉም የአማራ ህዝብ እንደማንም ኢትዮጱያዊ ጨዋና  በሰላም መኖር የሚፈልግ ህዝብ ሲሆን ከማህበረሰቡ እሴት ያፈነገጡ አንዳንድ የአማራ ተስፋፊ ሊሂቃን ግን የአማራ ህዝብ የሚያነሳውን የልማት የተጠቃሚነት እና ሌሎች የመብት ጥያቄዎቹን መመለስ ሲያቅታቸው በውሸት ትርክት ህዝቡን እያታለሉ የህልም እንጀራ እንደጠብቅ እያደረጉት ይገኛሉም ብለዋል፡፡

እነዚህ ሀይሎች የአማራን ህዝብ የማይጠቅሙ በመሆናቸው ወንድም ህዝባቸው ወደሆነው ወደ ትግራይ ህዝብ ከመዝመት ይልቅ ቁጥር አንድ ጠላታቸው ወደሆነው የአማራ እክራሪ ሊሂቃንና ተስፋፊ ሀይሎችን ነቅሶ በማውጣት ከሌላው የኢትዮጱያ ህዝቦች ጋር በሰላም መኖር አለባቸው ሲሉም ምክራቸውነ ለግሰዋል፡፡

ሄለን ሃፍቱ

Previous articleየአሜሪካ መንግስት በትግራይ፣ አፋርና አማራ ለሚገኙ ተረጂዎች ወደ 313 ሚልዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
Next articleየዓለም ማህበረሰብ ትኩረት ዩኩሬን ላይ በማድረጉ የኢትዮጵያ ቀውስ እየገዘፈ መምጣቱን Globnews.net ዘገበ፡፡