Home ዜና የአማራ ባለስልጠናት የትግራይ ተወላጆችን ከሰብአዊ እርዳታና ከመንግስታዊ አገልግሎት እንደከለከልዋቸውየዘገበው the Economist  የትግራይ...

የአማራ ባለስልጠናት የትግራይ ተወላጆችን ከሰብአዊ እርዳታና ከመንግስታዊ አገልግሎት እንደከለከልዋቸውየዘገበው the Economist  የትግራይ ተወላጆች ያመረቱትና ለውጭ ገበያ የተዘጋጀን የትግራይ ባለሀብቶች የሰሊጥ ምርት የአማራ ተወላጆች እንዲዘርፉትና እንዲያጓጉዙት ፍቃድና ዋስትና እንደሰጡዋቸው አመላክቷል፡፡

1100
0

በምዕራብ ትግራይ በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመው የዘር ማፅዳት ወንጀል በአገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነትን ሊያራዝመው   እንደሚችል  the Economist  ዘገበ፡፡

the Economist  እንደዘገበው የአማራ ባለስልጣናት በሀይል በወረሩት  የትግራይ ምእራብ ዞን መሬት አዲስ ሰፋሪዎችን በማምጣት መሬት እያከፋፈሉና የአማራ ማንነት የሚገልፅ መታወቅያ እያደሉ መሆናቸውን በዘገባው አመላክቷል፡፡

የአማራ ባለስልጠናት የትግራይ ተወላጆችን ከሰብአዊ እርደታና ከመንግስታዊ አገልግሎት እንደከለከልዋቸው  የዘገበው the Economist  የትግራይ ተወላጆች ያመረቱትና ለውጭ ገበያ የተዘጋጀን የትግራይ ባለሀብቶች የሰሊጥ ምርት የአማራ ተወላጆች እንዲዘርፉትና እንዲያጓጉዙት ፍቃድና ዋስትና እንደሰጡዋቸው አመላክቷል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን እና ተባባሪዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል ስለመፈፀማቸው የሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎች መውጣታቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡

በትግራይ ተዋላጆች ላይ የተካሄደው ጭካኔ የተሞላበት ዘመቻ የአብይ መንግስት እውቅናና ፍቃድ የተቸረው መሆኑን ያመለከተው ዘገባው የትግራይ ተወላጆች የትውልድ ቦታቸውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ በመስጠት  የእርሻ መሬታቸው አዳዲስ ለሰፈሩ አማራዎች እንዳከፋፈሉት ገልጿል the Economist  በዘገባው፡፡ 

በዚህ ዘመቻ በርካታ የትግራይ ተወላጆች በአማራ ተስፋፊ ሀይል በቤታቸው ውስጥና መንገድ ዳር እንደተገደሉ የዘገበው ዘኢኮኖሚስት

የአማራ ሚሊሻ በምርመራ ስራ ላይ ለተሰማራ ለአንድ የውጭ ዜጋ እዚህ ቦታ አንድም የትግራይ ሰው ማየት አንፈልግም  ብሎ መናገሩን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ደም አፋሳሽና ለ18 ወራት ያህል የዘለቀውና በትግራይ ላይ የታወጀው  ጀኖሳይድ ጦርነት የአብይ ቡድን እና ግብረአበረቹ በፈፀሙት ዘር በማፅዳት ወንጀል፣ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየደረሰባቸው መሆኑን the Economist  በዘገባው አመላክቷል፡፡

የአብይ ቡዱን በምእራብ ትግራይ ህዝብ የፈጸመው የዘር ማፀዳት ወንጀል ሽምጥጥ  አድርጎ ቢክድም የአማሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ቢሊንከን ከአንድ አመት በፊት በትግራይ ምእራባዊ ዞን በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማፅዳት ወንጀል መፈፀሙ  ይፋ ማድረጋቸው the Economist  በዘገባው አስታውሷል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመው ዘግናኝ ወንጀል ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን ባኖረው ከበባና ክልከላ ሳቢያ የጉዳቱ መጠን ለማጥናት ከባድ ቢያደርገውም እስከ አሁን አስደንጋጭ የሆነ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸው የትግራይ ተወላጆች አስከሬኖች መገኘታቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡

Amnistyinternational & human rights wotch  በጋራ ባወጡት ሪፖርት በመጥቀስ theEconomist  እንደዘገበው በትግራይ ምእራባዊ ዞን በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመው ወንጀል የአማራ ባለስልጣናት በተቀናጀ መንገድ  የፈፀሙ ወንጀል ነው፡፡ አመላክተዋል ብለዋል፡፡ ምንም አዲስ ሀሳብ ሳይጨመር እስከ አሁን ባለው በከበባውና ክልከላው ምክንያት አስደጋጭ የዘር ማፅዳት ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች፣ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህዝብን በጅምላ የማስራብ ወንጀል መፈጸሙ theEconomist  ያስረዳል፡፡

መብራህቱ ይባልህ   

Previous articleዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም ሰብኣዊ እርዳታ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ የአለም ማህበረሰብን  አወገዙ፡፡
Next articleየትግራይ ሴቶች ፆታዊ ጥቃት ፍትሕ እንዲያገኙ የፀጥታው ምክር ቤት ጠየቀ፡፡