Home ዜና የአማራ ተስፋፊዎችም የትናንቱ ስህተታቸው በመድገም አገሪቷንና ህዝቧን ወደ ከፋ እልቂት እያስገቡዋት መሆኑ...

የአማራ ተስፋፊዎችም የትናንቱ ስህተታቸው በመድገም አገሪቷንና ህዝቧን ወደ ከፋ እልቂት እያስገቡዋት መሆኑ ሙህራን ተናገሩ፡፡

978
0

የአማራ ተስፋፊ ሊሂቃን እያራመዱት ባለው የዘር ጥላቻ መሰረት ያደረገው ጦርነኝነት የሃገሪቱን ህዝቦች ለእልቂት፣ ለርሃብና ለከፋ ችግር ከመዳረግ አልፎ ሃገሪቷን ወደ መበታተን አፋፍ እያደረሷት መሆኑን ምሁራን ገልፀዋል፡፡

ምሁራኑ አያይዘውም የህዝቦች እልቂት ማብቂያ እንዲበጅለት የተፈለገ የሃይማኖት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች ከጦር ጎሳሚነት ወጥተው ሰላምን በመስበክ ለእውነት መቆም ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ሙሁራኖቹ በወቅታዊ ጉዳይ  ጋር በደረጉት ቆይታ የአማራ ተስፋፊዎች በየጊዜው እየነዙት ባለው ዘርን መሰረት ያደረገ ጥላቻ ህዝቦቿ ለእልቂት፣ ለረሃብና ለመፈናቀል እንዲዳረጉ የጎላ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

በእድገት ጎዳና ስትጓዝ የነበረችውና ለብዙ አፍሪካዊያን ተምሳሌት የነበረችውን አገርም ወደ ቁልቁለት እንድትጓዝና  በመበታተን አፋፍ ላይ እንድትደርስ አድርገዋታል ብለዋል፡፡

እነዚህ ተስፋፊዎች እንደቀደምት አባቶቻቸው ግዛትን ማስፋፋትና የስልጣን ህልማቸውን ለማሳካት የውሸት ትርክትን ዋነኛ ስራቸው አድርገው መያዛቸው አቶ ጎይቶኦም ተስፋማሪያም የተባሉ ምሁር አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም እየተካሄደ ባለው ጦርነት የሚማገዱት ወጣቶች የነሱ ልጆችና ቤተሰብ ሳይሆን የሚስክኑ ድሃ ልጅ መሆኑን በመግለፅ ህዝቡ በሃሰት ፕሮፖጋንዳው ሊታለል አይገባውም ብለዋል፡፡

እነዚህ ተስፋፊዎች በሚያቀነቅኑት ጥላቻ ተጠቃሚዎች እነሱ ብቻ በመሆናቸው አሁንም ህዝብን ከህዝብ ጋር ከማጋጨት ወደ ኋላ አላሉም ያሉት ደግሞ አቶ አለነ ሓጎስ የተባሉ ምሁር ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች በዋነኛነት ደግሞ የአማራ ህዝብ በልሂቃኖች የሃሰት ትርግት መወናበድ አይገባውም ያሉት ምሁሩ የተስፋፊዎቹ የጦርነት ነጋሪት አገሪቷን ወዴት እየወሰዳት እንደሆነ ሊያስተውሉ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ምንም ትርፍ የማይገኝ መሆኑ ሁሉም ሊረዳው ይገባል ያሉት ደግሞ አቶ ብርሃነመስቀል ፀሃዬ የተባሉ ሌላው ምሁር ሲሆኑ ችግርን በውይይት ለመፍታት ዝግጁነት ማሳየት የአርቆ አስተዋይነት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በፌዴራል መንግስት የሚተዳደሩና በየክልሎቹ ያሉት የመገናኛ ብዙሃንም ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩና ጦርነትን የሚቀሰቅሱ ስራዎች በመስራት አገሪቷ በገባችበት ምስቅልቅል ቤንዚን እየረጩ መሆናቸው አቶ ገብረመስቀል ተናግረዋል፡፡

እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን ከዚሁ ተግባራቸው ወጥተው ስለ ሰላም በመስበክ አገሪቷን እንድትረጋጋና ችግሮች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ በማድረግ ህዝቦቿም ከእልቂት አገሪታም ከመበታተን ለማዳን መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ለሰላም ቅድሚያ መስጠት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ብርሃነ መስቀል የአማራ ተስፋፊዎችም የትናንቱ ስህተታቸው በመድገም አገሪቷነና ህዝቧን ወደ ከፋ እልቂት ከማስገባት ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል፡፡

የሃይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎችም ጦርነትን ከመጎሰምና ወደ ጦር ሜዳ ሄደው ጦርነትን ከመባረክ ወጥተው ስለ ህዝባቸውና አገራቸው ሰላም ዋነኛ አጀንዳቸው ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

Previous articleየማህብራዊ ሚድያ ውሎ፡፡
Next articleየኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ምስራቅ እዝ በፋሽስቱ ቡድን ሀይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡