Home ዜና የአክሱም ሆስፒታል በመድሃኒትና የሕክምና ቁሰቁስ እጦት ምክንያት ግልጋሎት መስጠት ወደ ማይችልበት ሁኔታ...

የአክሱም ሆስፒታል በመድሃኒትና የሕክምና ቁሰቁስ እጦት ምክንያት ግልጋሎት መስጠት ወደ ማይችልበት ሁኔታ መድረሱን ተነገረ፡፡

943
0

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ባነረው ከበባና ክልከላ በመድሃኒት እጦት ምክንያት በርካታ ወገኖች በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ የአክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል አስታወቀ፡፡

ሆስፒታሉ በመድሃኒትና የሕክምና ቁሰቁስ እጦት ምክንያት ግልጋሎት መስጠት ወደ ማይችልበት ሁኔታ መድረሱንም ተገልፀዋል፡፡

አክሱማዊት ክንፈ ትባላለች በአክሱም ከተማ ተወልዳ ያደገች ስትሆን የ15 ዓመት ታዳጊ ናት፤ አክሱማዊት ባጋጠማት የልብ በሽታ በአክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ልታገኝ ብትመጣም ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ግብረ አበሮቹ ባኖሩት ከበባና ክልከላ በመድሃኒት እጦት ምክንያት ህይወትዋ በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንዳለ ትገልፃለች ፡፡

አክሱማዊት ክንፈ የገጠማት በሽታ በህክምና መዳን የሚቻል ቢሆንም የህክምና አገልግሎት ባለመግኘትዋ ህይወትዋ በከባድ አደጋ ላይ ወድቋል ይላሉ የህክምና ባለሞያ የሆኑት ሲስተር ኤልሳ በላይ ፡፡

በሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት መጥተው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ግብረአበሮቹ በፈፀሙት የጀኖሳይድ ጦርነት ሰለባ በመሆን መድሀኒት አጥተው ወደየ ቤታቸው የሚሸኙ የአክሱም እና አከባቢ ነዋሪዎች በርካቶች ናቸው፡፡

በሆስፒታሉ የፋርማሲ ባለ ሞያ የሆኑት አቶ ዳኒኤለ መብራህቱ በበኩላቸው  ታካሚዎች  በመድሃኒት እጦት የተነሳ ከሕመማቸው መዳን የሚችሉ ለሞት እየተዳረጉ ነው ይላሉ፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስከያጅ   እና የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር   የአክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ባጋጠመው የመድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ወደ ማይችልበት ደረጃ መድረሱን እና ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲያበጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መአዲ ሃይለ

Previous articleኤደን ገብረመድህን ትባላች የአስር አመት ታዳጊ ስትሆን መንቀሳቀስ የማትችል የመቐለ ከተማ ነዋሪ ናት፡፡ ገና የአንድ አመት ህጻን እያለች የጀመራት የጭንቅላት በሽታም እስካሁን መፍትሔ አላገኘም፡፡
Next articleፋሽስቱ የአብይ ቡድን በጋዜጠኞች ላይ እየፈፀመው ያለውን አፈናና እስራት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ዘገቡ፡፡