Home ዜና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ዛሬ መቐለ ገቡ፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ዛሬ መቐለ ገቡ፡፡

697
0

የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በቀጠናዊ ጉዳዮች ከትግራይ መንግስት ባለስልጣኖች ለመነጋገር ዛሬ መቐለ ከተማ ገቡ፡፡

የትግራይ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደገለፁት ልዩ መልእክተኛው ከትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋገረዋል፡፡

ኦባሳንጆ በትግራይ ላይ የተከፈተው የጀኖሳይድ ጦርነት ለማስቆም እና ሰላማዊ መፍትሔ ለማምጣት በተደጋጋሚ ወደ መቐለና አዲስ አበባ እየተመላለሱ የሰላም ጥረት እያደረጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

Previous articleወራሪ የኢሳያስ ሰራዊት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የከፈተው ጥቃት በጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከሸፈ
Next articleየአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት የሸራሮ ከተማን ለ23 ጊዜ በከባድ መሣሪያ መደብደቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አረጋገጠ።