Home ዜና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መግለጫ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መግለጫ

763
0

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ በምስራቅ ሸዋ በሸንኮራ ተስፋፊው የአማራ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ተከትሎ ዛቻ ያዘለ መግለጫ ማስተላለፉን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡
የፋሽስቱ ቡዱን አጫፋሪ የሆነው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ አፀፋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የገለፀ ሲሆን ድርጊቱን የሚያራግቡት የተስፋፊው ሃይል ሚዲያዎችንም አስጠንቅቋል በመግለጫው፡፡የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለተስፋፊዎች እድል ላለመስጠትና አገሪቷ የአክራሪዎች መፈንጫ እንዳትሆን አፀፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ማስወቁን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡
በክልሉ መንግስት በተደራጀውና በተስፋፊው የአማራ ሃይል የተፈፀመ ጥቃት መሆኑን የአለም መገናኛ ብዙሃን በስፋት በዘገቡበት ወቅት የሽመልስ አብዲሳ መንግስት ‘’ድርጊቱ በአክራሪዎች የተፈፀመ ነው’’ ብሎታል፡፡የራሱን ህዝብ መከላከልና ዋስትና መስጠት ያልቻለው የሽመልስ ቡዱን ድርጊቱን በሦስተኛ ወገን የተቀነባበረ ነው ለማለት የቀደመው የለም እንደ አዲስ ስታንዳርድ ዘገባ፡፡
ተስፋፊው የአማራ ሃይል አመራሮችና የፋሽስቶቹ ሳንባ የሆነው የአማራ ሚድያን ያስጠነቀቀው መግለጫው ተስፋፊ የአማራ ሃይሎች በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተከታታይ ጥቃቶች እያደረሱ በመሆናቸው ይህንኑ መከላከል የሚያስችል ስራ መስራት ይገባል ሲልም በመግለጫው አመላክቷል፡፡

Previous articleየትግራይ ህዝብ ጠላቶች የትግራይ ህዝብን የቅርስ ዘረፋና ውድመት ——
Next articleትክክለኛና ሃቀኛ ብሄራዊ እርቅ ከመጣ ለመደገፍና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸው ፕሮፌሰር  መረራ  ጉዲና ተናገሩ፡፡