Home ዜና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ምስራቅ እዝ በፋሽስቱ ቡድን ሀይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ምስራቅ እዝ በፋሽስቱ ቡድን ሀይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

1480
0

በምስራቅ ኦሮምያ በተካሄደው ጦርነት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ድል መቀዳጀቱን የእዙ የጦር  አዛዠ ሀምቢሳ ሲና ገልፀዋል፡፡

ሰራዊቱን ከምን ጊዜም በላይ በጠንካራ ቁመና ላይ እንደሚገኝም አዛዡ  ለOMN ቴሌቪዠን ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ማእከላዊና ደቡብ ኦሮምያ ላይ በስፋት ሲንቀሳቀስ የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በአሁኑ ወቅት በመላው ኦሮምያ እዝ አደራጅቶ የትጥቅ ትግሉን አጠናክሮ እንደቀጠለበት መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በፋሽስቱ ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊት ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ የሚገኘው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምስራቅ ኦሮምያ በተካሄደው ጦርነት ላይ ድል መቀዳጀቱን ነው የተገለፀው፡፡ 

የኦሮምያ ነፃነት ሰራዊት የምስራቅ እዝ ጦር አዛዠ የሆኑት ሀምቢሳ ሲና ለኦኤም ኤን ቴሌቪዠን እንደገለፁት ሰራዊቱ በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች እያደረገ ባለው  እንቅስቃሴ በፋሽስቱ ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊት ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡

በምዕራብ #ሐረርጌ ዞን ኦዳ ቡልቱም ወረዳ ሰራዊቱ በወሰደው እርምጃ 11 የፋሽስቱ ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊት የተገደሉ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችም መቁሰላቸውን ኣዛዡ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ሰራዊቱ በምስራቅ ሀረርጌ መልካ በድኡና ሌሎች ቦታዎች ላይ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አዛዡ ጠቁሞዋል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳርያዎችም ሰራዊቱ መማረኩን ለ omn አስታውቀዋል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ከኦሮሞ ህዝብ ልብ ውስጥ ለማውጣት ከፍተኛ ትግል አድርጓል ያሉት አዛዡ ይሁን እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ለኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያደረገ ያለውን ድጋፍ ይበልጥ ሰራዊቱን የሚያጠናክር እንደሆነ የኦሮምያ ነፃነት ሰራዊት የምስራቅ እዝ ጦር አዛዠ ሀምቢሳ ሲና ገልፀዋል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እስከወድያኛው በአንድ ወር ውስጥ አጠፋዋለሁ ብሎ መላው ኦሮሚያ የጦር አውድማ አድርጓታል፣ ፋሽስቱ ቡድን ጦርነቱ በአንድ ወር ውስጥ ይጠናቀቃል ቢልም ጊዜው ማለፉን ያስታወቁት አዛዡ ጦርነቱ አሁንም እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ የፋሽስቱ ቡድን በሁሉም አውደ ውግያዎች ሽንፈት እየተከናነበ መሆኑን አዛዡ አስታውቀዋል፡፡     

ሄለን ሃፍቱ

Previous articleየአማራ ተስፋፊዎችም የትናንቱ ስህተታቸው በመድገም አገሪቷንና ህዝቧን ወደ ከፋ እልቂት እያስገቡዋት መሆኑ ሙህራን ተናገሩ፡፡
Next articleAmnisti international and Human rights wotchs የጋራ ሪፖርትን በተመለከተ  የታዩ ህፀፆችን እንዲስተካከል  ተጠየቀ፡፡