Home ዜና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ትግል በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ድል መቀናጀቱ ተነገረ፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ትግል በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ድል መቀናጀቱ ተነገረ፡፡

1071
0

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የፋሽስቱ ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊትና ግብረ አበሮቹን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ በተለያዩ ኦሮምያ አካባቢዎች ላይ ድል መቀዳጀቱን የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ገለፁ፡፡የፋሽስቱ ቡድን ቀነገደብ አስቀምጦ እናጠፋቸዋለን የሚለው መፈክሮች እንደማይሳካና ኦሮምያ ውስጥ ያለው ይህ ጨቋኝ ስርአት እስኪደመሰስ ድረስም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል አቀባዩ አረጋግጠዋል፡፡

የፋሽስቱ ቡድን ከፍተኛ አመራሮችና ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ላለፉት ሶስትና አራት አመታት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እናጠፋለን በማለት የጊዜ ገደቦችን በማስቀመጥ ኦሮምያ ላይ በተደጋጋሚ ጦርነት ሲያውጁ ቆይተዋል፡፡ይሁንና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ በጦር መሳርያና በሰውሀይል ስልጠና እያየለ በመምጣት በርካታ ቦታዎችን በመቆጣጠሩ የፋሽስቱ ቡድን እንዳሰበው እቅዱ ሊሰምርለት ባለመቻሉ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቶታል፡፡

ታድያ የፋሽስቱ ቡድን እንደተለመደው አሁንም ከአራት አመት በኋላ ከተስፋፊው የአማራ ሀይልና ከአምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት የኦሮምያ የፀጥታ ሀይሎችን ጨምሮ ፀረ ሽምቅ ኦፕሬሽን ብሎ የሰየመውን ጦርነት አውጇል፡፡ ጦርነቱም ተስፋፍቶና ተጠናክሮ መቀጠሉን በተለያዩ ምንጮች እየተገለፀ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በበኩሉ ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገሩን የገለፁት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ የፋሽስቱ ቡድን ከዚህ ቀደምም ተደጋጋሚ በ30 እና 15 ቀናት ውስጥ እናጠፋቸዋለን ሲል መክረሙን አስታውሰው የአሁኑ ዘመቻም ከበፊቱ የሚቀይረው አንዳች ነገር አይኖርም ብለዋል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በጠንካራ ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል ያሉት የሰራዊቱ ቃል አቀባይ የፋሽስቱ ቅጥረኛ ሰራዊትን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ቃል አቀባዩ አያይዘው በሰጡት መረጃ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያና ወንጪ አካባቢዎች ላይ ሰራዊቱ ድል መቀዳጀቱን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በግንደበረት የተሰማራው የሪፐብሊካን ጋርድ ስምሪት ከጥቅም ውጪ መደረጉን አክለዋል፡፡ይህ በንዲህ እንዳለ የፋሽስቱ ቡድን የሶማሌ ክልል የፀጥታ ሀይሎችን በደቡብ ኦሮምያ ማሰማራቱን ገልፀዋል፡፡የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ኦሮምያ ውስጥ ያለው ጨቋኝ ስርአት እስኪደመሰስ ድረስ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ዊንታ ዘላለም

Previous articleለዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መርማሪ ኮሚሽን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲተባባር የአውሮፓ ህብረት ጠየቀ፡፡
Next articleሰብአዊ መብት ተማጔቾች የምርመራ ሪፖርት አሳማኝ ነገር የያዘ መሆኑ ምሁራን እየገለፁት ይገኛሉ፡፡