Home ዜና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም ከካዛኪስታን ብሄራዊ የህክምና ሳይንስ...

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም ከካዛኪስታን ብሄራዊ የህክምና ሳይንስ ዩኒቨርስቲ የክብር የፕሮፌሰርነት ማአረግ ተበረከተላቸው፡፡

539
0

ዶክተር ቴድሮስ የክብር የፕሮፌሰርነት ማአረግ የተቀበሉት መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ማህበረሰብ የሚለውን የአልማ አታ ዲክላሬሽን ዓለም አቀፋዊ ስምምነት ሆኖ እንዲተገበር  ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከነበራቸው የቀድሞ የካዛኪስታን ጤና ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ሻርማኖቭ እጅ መሆኑን በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አጋርተዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ በጤናው ዘርፍ ላይ ለጋሲያቸውን ለአለም ማህበረሰብ በማበርከታቸው ከፍተኛ ምስጋና እንዳላቸው ዶ/ር ቴድሮስ በማህበራዊ ትስስራቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

የአልማ አታ ዲክላሽን ተደራሽነት መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ለሁሉም የሚለው ለሰዎች ጤና መጠበቅ መሰረታዊ መሆኑን የጠቀሱት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተሩ፣ የካዛኪሰታን ጤና ሚኒስትር ዶክተር አዝሃር ጊኒያት መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ለማዳረስ እየሰጡት ያለውን አመራርና ጥበብ አመስግነዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም በጤና ዘርፍ ለአለም ማህበረሰብ እያበረከቱት ያለውን ሙያዊ አስተዋፅኦና የአመራር ጥበብ ከስኮትላንድ ኤደን በርግ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ሽልማት ተበርክቶላቸው እንደነበር ይታወሳል።

ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ሆነው እያበረከቱት ያለውን የአመራር ብቃት በማድነቅ በያዝነው አመት የክብር ማአረግ ሲሰጣቸው የአሁኑ ለሶስትኛ ጊዜ ነው።

በተመሳሳይ ዶ/ር ተድሮስ ኡቡንቱ የተሰኘ የሰብአዊነት የክብር ሽልማት ከደቡብ አፍሪካ መሸለማቸው የሚታወስ ነው።

Previous articleፋሽስቱ የአብይ ቡድን የኢሳያስ ሰራዊት እንዲሁም የተስፋፊው የአማራ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት ካወጁበት ጥቅምት 2013 ዓ.ም አንስቶ በትግራይ ህዝብ ላይ በርካታ ዘግናኝ ግፎች መፈፀማቸው ያስታውሰው የትግራይ ውጭ ግንኙነት ፅ/ቤት የተፈፀሙ ግፎች የሚያጣራ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዳይቋቋም ሲከላከሉ መቆየታቸው በአንፃሩ የትግራይ መንግስት ገለልተኛ መርማሪ አካል እንዲቋቋም በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን ያትታል።
Next articleእጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ተገድሎ ወደ ተከዜ ወንዝ የተጣለ የአንድ የትግራይ ተወላጅ አስከሬን መገኘቱን ተዘገበ፡፡