Home ዜና የዛላንበሳ እናቶች ሰቆቃ

የዛላንበሳ እናቶች ሰቆቃ

በኤርትራ ወታደሮች የጅምላ ፆታዊ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል የ7 ልጆች እናት የሆነችው የትግራይ ዛላንበሳ ከተማ ነዋሪ እናት ዛሬ ላይ ከቀየዋ ተፈናቅላለች:: ሌላኛዋ ወጣት ከወራሪዎቹ ሰይጣናዊ ድርጊት ለመሸሸ የዚህ ሰለባ ናት:: የአምበገነኖች ቁንጮ የሆነው በኤርትራው ኢሳያሰ አፈወርቂ በትግራይ ጠል ተረት ተረት ያደገውና ኑሮውን ከቀበሮ ጉድጓድ ሳይላቀቅ ያደገው ሰራዊት፣ በትግራይ ምድር ለዓለማችን እንግዳ የሆኑ አሰቃቂ ግፎችን ፈፅመዋል:: ዛሬ ላይ ቀየዋን ጥላ ከመሰደዷ በፊት በተደጋጋሚ ወረራ የደቀቀችው ዛላምበሳ ከተማ ነዋሪ የነበረችው የ7 ልጆች እናት ሕዳር 3/2013 ዓ/ም ሰለገጠማት ዱቡዳ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንዲህ ስትል ገልፃልች:: ያኔ ሳምንት ያስቆጠረውን ጦርነት እንዳመጣህ መልስልን ስትል ፈጣሪዋን ተማፅና ወደ ቤቷ ትመለሳለች:: እንደወትሮው የቤትዋን በር ከፍታ ወደ ውስጥ ስትገባ የገጠማት ነገር ግን በህይወቷ ኣይታው የማታውቀው እጅግ አስድንጋጭ እና አሳዛኝ ክስተት ትላንት የተፈጠረ ያህል ታሰታውሰዋለች:: በሰማችው አስድንጋጭ አረመኔያዊ ተግባር ከዛላምበሳ ወደ አዲግራት የሸሸችው ሌላኛዋ ወጣትም ከእነ ሰይጣናዊ ተግባራቸው ተከትለዋት ወደ አዲግራት ከተማ በገቡት የኤርትራ ወታደሮች በሌሎች ላይ ሲፈፅሙት የተመለከተችውና የፈራችው ነውረኛ ተግባራቸው አልቀረላትም:: እነኚህን እንደ ምሳሌ አነሳን እንጂ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሀይሎች በትግራይ ምድር ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ፃታዊ ጥቃት ፈጣሪ ይቁጠረው:: በዘንድሮው #ዓለም አቀፍ የማርች 8 የሴቶች ቀን የትግራይ ሴቶች ሰቆቃ የአለም አጀንዳ ሆኖ መከበሩ መልካም ቢሆንም የትግራይ እንስቶች እምባ ለማበስ ወንጅለኞቹ ወደ ሕግ ማቅረብ ይገባል ብለዋል የጥቃቱ ሰለባዎች። በሄለን ወ/ ዮሃንስ

1115
0

Previous articleየአሜሪካው ሰኔት በፋሽስቱ የአብይ ቡድንና አምባገነኑ የኢሳያስ መንግስት ላይ አዲስ ማእቀብ ለመጣል የሚያስችል ረቂቅ ህግ S.3199 አፀደቀ፡፡
Next articleየአብይ ቡድን ለማካሄድ ያቀደውን ሃገራዊ ምክክር ገና ከጅምሩ ሞቷል ሲል የአፍሪካን አርጉመንትስ ገለፀ፡፡