Home ዜና የፋሽስቱ ቡድን ያቀረበው ክስ መሰረት እንደሌለው የትግራይ የውጭ ጉዳይ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

የፋሽስቱ ቡድን ያቀረበው ክስ መሰረት እንደሌለው የትግራይ የውጭ ጉዳይ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

955
0

የሰብኣዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ የትግራይ ሰራዊት እንቅፋት እንደሆነ በማስመሰል የፋሽስቱ ቡድን ያቀረበው ክስ መሰረት እንደሌለው የትግራይ የውጭ ጉዳይ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡
የፅ/ቤት ከፍተኛ ሃላፊ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እሰከአሁንም የትግራይ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው ኣካባቢዎች ሰብኣዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እንደሌሉ ገልፀዋል።
የትግራይ መንግስትና የፋሽስቱ የኢትዮጵያ መንግስት ግጭቶችን በጊዜያዊነት በማቆም ወደ ትግራይ ያለተገደበ የሰብኣዊ እርዳታ ለማሰገባት ውሳኔ ላይ ቢደረሱም እስከ ዛሬ ወደ ትግራይ የገባ ምንም ዓይነት የሰብኣዊ እርዳታ የለም ብሏል።
ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ወደ ትግራይ ይገባል የተባለው የሰብኣዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች የትግራይ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሳይደርሱ የትግራይ ሰራዊት እንቅፋት እንደሆነ በማስመሰል የትግራይ መንግስትን ለመክስስ መቻኮሉ የተለመደውን ማጭበርበሩ ግልፅ ያደረገ ነው ብለውታል።
ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው ጀኖሳይድ ቅጥያ የሆነው ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ የመጠቀም እና ለሁለተኛ ዙር ወረራ እየተዘጋጀ መሆኑ የሚነገርለት የፋሽስቱ ቡድን ጊዜ መግዣ እና መሰረት የሌለው ክስ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።
ሶስተኛ ወገን ባለበት የተደረሰው ጊዚያዊ የግጭት ማቆም ሰምምነት በፋሽስቱ ቡድን እየተጣሰው ነው ያለው የትግራይ የውጭ ግንኙነት ፅህፈት ቤት በስምምነቱ መሰረት ወደ ትግራይ ይገባል የተባለው የሰብአዊ እርዳታ በአስቸኳይ የማይገባ ከሆነ የትግራይ መንግስት ሌላ አማራጭ ለመውሰድ እንደሚገደድ ፕሮፌሰር ክንደያ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋዕ።

Previous articleአለም አቀፍ የተጋሩ ባለሙያዎችና ምሁራን የአቋም መግለጫ
Next articleበትግራይ ላይ የተፈፀመው የቤተ እምነት ውድመት አወደ-ርእይ ማሳያ—