Home ዜና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ባኖረው ከበባ እና ክልከላ   እናቶች እና...

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ባኖረው ከበባ እና ክልከላ   እናቶች እና ህፃናት  ለሞት አደጋ እየተጋለጡ መሆናቸው ተነገረ፡፡

3560
0

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የመድሃኒት እና የአምቡላንስ አገልግሎት  በመቋረጡ ምክንያት እናቶች እና ህፃናት  ለሞት አደጋ እየተጋለጡ መሆናቸው የትግራይ ደቡባዊ ዞን መኾኒ ከተማ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡

ወ/ሮ ሕልፍቲ ዓለም ትባላለች በደቡብ ትግራይ ዞን የራያ አዘቦ ወረዳ ማርሳ ቀበሌ ነዋሪና የ 3 ልጆች እናት ነች ፡፡

ከአሁን በፊት ሁለት ልጆችዋ ስትወልድ  በቂ የህክምና አገልግሎት አግኝታ በሰላም ብትወልድም አሁን ላይ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ባወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት  እንደ ማንኛውም ትግራዋይ ተጠቂ ሆናለች፡፡

በተጨማሪ ሶስተኛ ልጇን ለመውለድ በተቃረበችበት ወቅት የጀኖሳይድ ጦርነቱ ባስከተለው ውደመት ተከትሎ በመኾኒ ሆስፒታል የአንቡላንስ አገልግሎት ባለሞኖሩ በቤቷ ለመውለድ  መገደዷን እናቷ ወ/ሮ አከዛ ይናገራሉ፡፡

የሆስፒታሉ የህክምና ባለሞያዎች በበኩላቸው እኛ እንደ በለሞያ ህዝባችን ለማገልገል  በተቋማችን ብንገኝም  የአንቡላንሰ አገልግሎት ጨምሮ በሆስፒታሉ  የመድሀኒት አቅርቦት በለመኖሩ እናቶች ለተለያዩ አደጋ እየተጋለጡ  በመሆናቸው አሳዛኝ ነው ይላሉ፡፡

የመኾኒ ሆስፒታል ስራ አስከያጅ  አቶ ሙሉጌታ ረዳኢ በበኩላቸው  ፋሽስቱ ቡድን ባኖረው ክልከላ ምክንያት  ተቋማችን  የመድሀኒት አቅርቦት ስለሌለው  በተለይ ደግሞ  ለእናቶች እና ለህፃናት የሚደረገው የህክምና ክትትል  በመቋረጡ እናቶች በቤታቸው እየወለዱ በመሆናቸው ሞትን ጨምሮ ለተለያዩ ከፍተኛ አደጋ እየተጋለጡ ነው ብለዋል ፡፡

የእናቶች እና ህፃናት ሞት መቀነስ የሁሉም ሀላፊነት ነው የሚሉት አቶ ሙሉ ጌታ ረዳኢ በትግራይ እናቶች እና ህፃናት በአጠቃላይ በትግራይ ህዝብ እየደረሰ ያለው ግፍ የአለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ  ሊያወግዘው  እና አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጥበት ይገባል ብለዋል፡፡

መአዲ ሃይለ

Previous articleየካናዳ መንግስት በፋሽስት የአብይ ቡድን ላይ ማእቀብ እንዲጥል አንድ የካናዳ ምክር ቤት አባል ጠየቁ፡፡
Next articleበረሃብ ቸነፈር  ህዝቦቿ ከሚጠቁባቸው ሦስት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ  በግንባር ቀድምትነት እንደምትገኝ አየርላንድ የሰብአዊና ልማት ድርጅቶች የጋራ ጥምረት አስታወቀ፡፡