Home ዜና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በጋዜጠኞች ላይ እየፈፀመው ያለውን አፈናና እስራት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ...

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በጋዜጠኞች ላይ እየፈፀመው ያለውን አፈናና እስራት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ዘገቡ፡፡

1081
0

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፋሽስቱ ቡድን እያካሄደው ባለው አፈናና እስራት 16 ጋዜጠኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ታውቋል፡፡

Al-jazeera  እና አዲስ ስታንዳርድ የታሰሩት ጋዜጠኞች ቤተሰቦች እና ጠበቃዎቻቸውን አነጋግረው እንደዘገቡት ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የእስራት እና አፈና እርምጃውን እየወሰዱ ያሉት በሃገሪቱ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ለማፈንና ፋሽስቱ ቡድን በየእለቱ በሰላማዊያን ዜጎች ላይ እየፈጸመው ያለውን ግድያ፤ የጅምላ እስራትና ስወራ እንዲሁም በየአከባቢው ያወጀውን ጦርነት እንዳይታወቅበት ለማፈን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፋሽስቱ የአብይ ቡድን የጸጥታ ሃይሎች እየታደኑ ለእስርና አፈና እየተዳረጉ ያሉት የሰላ ነቀፌታ የሚያቀርቡ አንጋፋ ጋዜጠኞች  እና በጋዜጠኝነት ተዘማጅ የሞያ ዘርፎች የተሰማሩ አካላትን ያጠቃለለ እንደሆነ ዘገባዎቹ አመልክቷዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የሚውሉ የሚድያ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች ሁኔታ ለማወቅ የፋሽስቱ ቡድን የጸጥታ ሃይሎች ሲጠየቁም ምንም ዓይነት መረጃ እንደማይሰጡ ቤተሰቦቻቸውና ጠበቃዎቻቸውን በመጠየቅ መገንዘብ እንደቻሉ Al-jazeera እና አዲስ ስታንዳርድ በዘገባቸው አስታውቀዋል፣፣

አንዳንድ የጸጥታ ሃይሎች ደግሞ ጋዜጠኞቹ የታሰሩበት ምክንያት ሲጠየቁ በፋሽስቱ ቡድን ባለስልጣናት ትእዛዝ እንደሆነ መግለጻቸውን ነው የሚድያ ተቋማቱ የዘገቡት፡፡

የጋዜጠኞች እስር እና አፈና በመካሄድ ላይ ያለው አብዛኛው በሃገሪቱ መዲና አዲስ አበባ ና ባህርዳር ከተሞች ውስጥ ነው፡፡

ሰሞኑን እየታፈኑና ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በጸጥታ ሃይሎቹ እየታሰሩ የሚገኙት ጋዜጠኞች አብዛኛዎቹ ቀደም ሲልም ለወራት ታስረው እና ለዘገባ የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች ተቀምተው ከእስር እንዲለቀቁ የተደረጉ እንደሆኑ ዓለም አቀፍ የሚድያ ተቋማቱ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነትን በማፈን ከሚጠቀሱ ሃገራት መካከል በግንባር ቀደምትነት ተርታ ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡

የዜና ምንጮቻችን አዲስ ስታዳርድ  Al-jazeera  እና ለጋዜጠኞች ህጋዊ ከላላ የሚሰጠው cpj ናቸው፡፡

አማረ ኢታይ  

Previous articleየአክሱም ሆስፒታል በመድሃኒትና የሕክምና ቁሰቁስ እጦት ምክንያት ግልጋሎት መስጠት ወደ ማይችልበት ሁኔታ መድረሱን ተነገረ፡፡
Next articleኢትዮጵያውያን እናቶች እንደ ሶማሊያውያን እናቶች በትግራይ ጦርነት  የሄዱ ልጆቻችን የት ገቡ ብለው ሊጠይቁ ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡