Home Uncategorized ፋሽስቱ የአብይ ቡድን አገሪቷን ወደ ጦርነት በማስገባቱ የአገሪቱ ብር የመግዛት አቅምም በ26%...

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን አገሪቷን ወደ ጦርነት በማስገባቱ የአገሪቱ ብር የመግዛት አቅምም በ26% ወርዷል ተባለ፡፡

868
0

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በአሜሪካ ከቀረጥ ነፃ ገበያ እድል መከልከሏን ተከትሎ በአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ማጋጠሙንና በጥቁር ገበያ የአንድ ዶላር ምንዛሪ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ Bloomberg ዘገበ፡፡

የአገሪቱ ብር የመግዛት አቅምም በ26 በመቶ ወርዷል ተብሏል፡፡ ያለው ዘገባው የዶላር ምንዛሪው መናር አገሪቷን ወደ ጦርነት በማስገባቱ የተወሰደባት እርምጃ የኢኮኖሚ ቀውስ ውጤት መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ቢገልፁም Bloomberg ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ግን ምክንያቱን የሚገልፅላቸው አካል አለማግኘታቸው ያስረዳል፡፡

ለውጭ ምንዛሪው መናር በዋነኛነት ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ባለው ጦርነት ተከትሎ አገሪቷን ወደ አሜሪካ ገበያ ለማስገባት ተፈቅዶላት የነበረው ከቀረጥ ነፃ ገበያ እድል በመከልከሏ ምክንያት ባጋጠማት የምንዛሪ እጥረት ነው ብሏል Bloomberg  የፋሽስቱ ቡዱን የአለምን ማህበረ-ሰብ እያጭበረበረ የገዛ ህዝቡን እየጨፈጨፈ በመሆኑ ብድርና እርዳታ ሲያደርጉለት የነበሩት አገራትና ተቋማት እጃቸውን መሰብሰብ መጀመራቸው ሌላው ምክንያት መሆኑን ድረገፁ አስነብቧል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የከፋ ድርቅ በማጋጠሙና በአገሪቱ እየተንሰራፋ ያለው የኮረና ቫይረስ ስርጨትና ሌሎቹ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸው ቡሉምበርግ ባወጣው ዘገባ አስረድቷል፡፡

የፋሽስቱ ቡዱን የቀኝ እጅ የሆነው ብሄራዊ ባንክ በበኩሉ አጋጥሞ ያለውን የዋጋ ንረትና የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎች ለመውሰድ መዘጋጀቱን ቀደም ሲል መግለፁ ቡሉምበርግ በዘገባው አውስቶ፡፡አንድ የውጭ ባለሃብት መንግስት ገበያውን በሙሉ በመቆጣጠሩ ምክንያት የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት አለመቻላቸው በመግለፅ ባገኙት  እድል ሁሉ ወደ ጥቁር ገበያው ገብተው ለመስራት  መገደዳቸው ለድረገፁ አስረድተዋል፡፡

በጥቁር ገበያ ምንዛሪ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የአገሪቱ ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ምንዛሪን ለመቆጣጠር የሚያስችለው አቅም ተሽመድምዷል ተብሏል፡፡

የአገሪቱ ማእከላዊ ስታትስቲክስ ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ የአገሪቱ ዜጎች በምግብና በነዳጅ የዋጋ ግሽበቱ በ37 በመቶ በመጨመሩ ለውጭ ምንዛሪው መናር እንደ ምክንያት ያስቀመጠ ሲሆን ለዚህም በሩሲያና በዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት የፈጠረው ነው በማለት ህዝብን ለማታለል እየሞከረ መሆኑን ቡሉምበርግ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አገሪቷ ከሰባት አመታት በፊት በርበራ ወደብን ለመገንባት ገብታው የነበረው የ19 በመቶ ድርሻ ማቋረጧን የሶማሊላንድ መንግስት መግለፁን ዘ-ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ይህም በአገሪቱ ተጨማሪ  በእንቅርት ላይ ጀሮ ደገፍ መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን አስተያየትን ጠቅሶ ብሉምበርግ በዘገባው አትቷል፡፡

በተካ ጉግሳ  

Previous articleየትግራይን ቀውስ እንዲያበቃ ሁሉም በጋራ ድምጻችን ማሰማት አለብን – ሳማንታ ፓወር
Next article‘Escaping Eritrea’ የተሰኘ  በፍሮንትላይን የቀረበው ዶክመንታሪ ፊልም የፒቦድይ አዋርድ አሸናፊ ሆነ፡፡