Home ዜና ፋሽስት አብይ በትግራይ ህዝቡ በረሃብ እንዲያልቅ አስቀድሞ በማቀድ የፈፀመው ተግባር ነው ስትል...

ፋሽስት አብይ በትግራይ ህዝቡ በረሃብ እንዲያልቅ አስቀድሞ በማቀድ የፈፀመው ተግባር ነው ስትል አክቲቪስት ምልእተ ገለፀች፤

639
0

የፋሽስቱ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ እያደረሰ ካለው ጥፋት ለግብርና ስራ የሚያገልግሉትን በማውደም  ስትል አክቲቪስት ምልእተ ብርሃነመስቀል ሴንተር ፖይንት ከተባለ  ቴሌቭዢን ጋር ባደረገችው ቆይታ ገለፀች፡፡

የፋሽስቱ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄደው እኗ አሁንም እየፈፀመው ያለው ጭፍጨፋና በአስከፊ ረሃብ የማሰቃየት ተግባር አስቀድሞ ያቀደው ተግባር መሆኑን የማህበራዊ ሚዲያ ንቁ ተሳታፊዋ ምልእተ ብርሃነመስቀል አስረድታለች፡፡

አክቲቪስት ምልእተ ብርሃነመስቀል ሴንተር ፖይንት ከተባለ  ቴሌቭዢን ጋር በነበራት ቆይታ ፋሽስታዊያንና የአማራ ተስፋፊዎች ለ19 ወራት ያህል የትግራይ ህዝብ እንዲገደልና እንዲጨፈጨፍ ከማድረጋቸውም በላይ ከዚሁ ጭፍጨፋ የተረፈው ህዝብም  ማንኛውም አገልግሎት እንዳያገኝ በማድረግ በአለም አስከፊ የሆነውን ኑሮ እንዲመራ እያስገደዱት ይገኛሉ ብላለች፡፡

አስቀድመው ትግራይን በሁሉም መንገድ ከአለም እንዳይገናኽ ነው ያደረጉት፤ በትግራይ ምንም አይነት አገልግሎት እንዳይኖር አድርገዋል፤ በዚህም ከሰባት ሚልዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ከ19 ወራት በላይ ለከፋ ችግር ተዳርጎ ይገኛል፤ ከሞት የቀረውም ቢሆን ምንም አይነት መብራትም ሆነ ስልክ እንዲያገኝ አልተደረገም በዚህም የገጠመውን መከራና ስቃይ እንኳ የሚገልፅበት እድል አላገኘው፡፡

የትግራይ ህዝብ በረሃብ አሰቃይቶ ለመግደል ያለመው የፋሽስቱ ቡዱን ህዝቡን ከመጨፍጨፍና በአስከፊ ረሃብ እንዲሰቃይ ከማድረግ በተጨማሪ የአርሶ አደሮች የእርሻ መሳሪያዎች በማውደም አስከፊ በደል ሲፈፅሙ መቆየታቸው አክትቪስቷ አስረድታለች፡፡

እንዲሁም ከግድያና ጭፍጨፋ የቀሩት አርሶ ደሮች ለግብርና ስራ የሚጠቀምባቸው በሬዎች አርደው በመብላት ከእርሻ ስራ ውጭ እንዲይሆኑ በማድረግ ከለመዱት የግብርና ስራ በማስተጓጎል ለከፋ ስቃይ እና ርሃብ እንዲዳረጉ አድርጓል ብላለች፡፡

የፌዴራል ወታደሮች የአርሶአደሩን የእርሻ መሳሪያዎች በመሰባበርና በማቃጠል አውድመዋቸዋል፡፡ወደ ገጠራማው የትግራይ አካባቢ የእርዳታ እህል እነዳይደርስም ነዳጅ በመከልከል ለከፋ ረሃብ እንዲሰቃይ እያደረገ ነው፡፡ ይህም የአለም ማህበረሰብ የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ በፋሽስቱ ቡዱን እና በተስፋፊው የአማራ ሃይሎች እንዲሁም የአምባገነኑ የኢሳያስ ወታደሮች ከደረሰበት እልቂትና ጭፍጨፋ በተጨማሪ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ወደ ሱዳን በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ እዛው ትግራይ ውስጥ  መፈናቀላቸው የቴሌቭዥን ጣብያው ዘግቧል፡፡

የፋሽስቱ ቡዱን አጋዠ ሃይል ከውጭ ጋብዞ በትግራይ ህዝብ ላይ ካደረሰው በደል በተጨማሪ የትግራይ ቅርሶችና የእምነት ተቋማት እንዲወድሙ ማድረጉን የዘገበው የቴሌቭዥን ጣብያው በመቶ ሺዎች ሰላማዊያን ሰዎች ያለቁበት ይሀው ጦርነት እያለ አለም ወደ ዩክሬን ማዘንበሉ አስረድቷል፡፡

የአለም ተማራማሪዎች እስካሁን ባደረጉት ጥናት ከ500ሺህ በላይ ሰላማዊያን ሰዎች ያለቁበት የትግራይ ጦርነት እያለ አለም ስለ ዩክሬን ጦርነት እያስጨነቃት ነው ብሏል፤ የኦርቶዶክስ ተከታዮች በብዛት ኢላማ የተደረጉበት ይሀው ጭፍጨፋ አንዳንዶቹ ጀኖሳይደ መሆኑ እየገለፁ ይገኛሉ

ተካ ጉጉሳ 

Previous articleፋሽስት የአብይ ቡድን በማንነታቸው ምክንያት በተለያዩ ማጎሪያ ካምፖች እያሰቃያቸው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ /GSTS/ ጠየቁ፡፡
Next articleEU ኮሚሽን ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ካላስጀመረ ምንም ዓይነት የፋሽናንስ በጀት ድጋፍ እንደማያደርግ አስታወቀ።