Home ዜና ፋሽስት አብይ አሕመድ በትግራይ ህዝብ ላይ ፍፁም ረሃብ የሚባል ነገር የለም በማለት...

ፋሽስት አብይ አሕመድ በትግራይ ህዝብ ላይ ፍፁም ረሃብ የሚባል ነገር የለም በማለት መካዱን የዓለም ሰላም ድርጅት አጋለጠ፡፡

1010
0

በትግራይ ህዝብ ላይ በአስር አመታት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ ከፍተኛ ሰው ሰራሽ ረሃብ ቢከሰትም ፋሽስት አብይ አሕመድ ግን በትግራይ ህዝብ ላይ ፍፁም ረሃብ የሚባል ነገር የለም በማለት መካዱን the Organization for World Peace ዘገበ፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ ለ19 ወራት ያህል የቀጠለውን ግልፅ የጀኖሳይድ ጦርነት በሰው ሰራሽ ረሃብ እና ህክምና መድሃኒት እጦት ምክንያት በሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እያሻቀበ ነው ሲል the Organization for World Peace የተባለ ድረገፅ ዘግበዋል፡፡

ድረ-ገፁ የትግራይ ጦርነት በጥንታዊ ማህበረ-ሰቦች ላይ ያደረሰው ተፅኖ በሚል ርእስ ባወጣው ዘገባ ጦርነቱ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት ሂደት አመሰቃቅሎታል ብሏል፡፡

ፋሽስት የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጀውን ግልፅ ጦርነቱን ተከትሎ ፆታዊ አመጽ ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ቀጥታ ግድያ ሰው ሰራሽ ረሃብ በመፍጠር ህዝብን በረሃብ እንዲያልቅ እና ሌሎች ወንጀሎችን በትግራይ ህዝብ ላይ መፈፀሙን ዘገባው አመላክቷል፡፡

በፋሽስቱ ወታደሮችና በተስፋፊ የአማራ ታጣቂ ሀይል ከ50,000 እስከ 100,000 የሚደርስ የትግራይ ህዝብ ቀጥታ ግድያ እንደተፈፀመበት ያመላከተው ድረ ገፁ ከ150,000 እስከ 200,000 የሚደርስ ህዝብ ደግሞ በከበባውና ክልከላው ተከትሎ በተፈጠረ ረሃብ ለሞት ተዳርጓል ብሏል፡፡

በከበባውና ክልከላው ምክንያት ተገቢው የጤና ክብካቤና የህክምና መድሃኒት እጦት ምክንያት ደግሞ አንድ መቶ ሺህ የትግራይ ህዝብ ለህልፈት መዳረጉን ድረ ገፁ በዘገባው አመላክተዋል፡፡

በትግራይ ህዝብ በአስር አመታት ውስጥ ተከስቶ የማያቅ ከፍተኛ ሰው ሰራሽ ረሃብ መከሰቱን ያመላከተው ድር ገፁ ፋሽስት አብይ አሕመድ ግን በትግራይ ረሃብ የሚባል ነገር አልተከሰተም በማለት መካዱን ድረ ገፁ ዘግቧል፡፡

ድረ ገፅ የአይን እማኞችን በመጥቀስ እንደዘገበው የፋሽስቱ አብይ ወታደሮች የትግራይ አርሶ አደሮችን ንብረት የሆነውን ሰብል ዘርፈው በመውሰዳቸው ህዝቡ ለከፋ ረሃብ እንዲጋለጥ አንዱ ምክንያት ነው፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የእርደታ እህልና የህክምና ቁሳቁሶች እንዳይገባ በመከልከሉ በሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ድጋፍ እንዳያገኝ አድርጎታል ብሏል፡፡

Previous articleየትግራይ ፖሊስ ኮምሽን አዲስ ምልምል ፖሊሶች አስመረቀ።
Next articleበዓለማችን በሚገኙ 20 ሃገራት ውስጥ እጅግ የከፋ ረሃብ ሊከሰትባቸው እንደሚችል የዓለም OCHA እና WFP አስጠነቀቁ፡፡