Home ዜና ፋሽስት የአብይ ቡድን በማንነታቸው ምክንያት በተለያዩ ማጎሪያ ካምፖች እያሰቃያቸው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች...

ፋሽስት የአብይ ቡድን በማንነታቸው ምክንያት በተለያዩ ማጎሪያ ካምፖች እያሰቃያቸው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ /GSTS/ ጠየቁ፡፡

514
0

ዓለም አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሞያዎች  ማህበረ-ሰብ  GSTS ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና ሚሸል ባችሌትና የበዘፈቃድ አስር ቡድን ልዩ መርማረ ሊቀመንበር  ፕሮፌሰር ሚርያም ኢስትራዳ ካስቲሎ በጻፉት ደብዳቤ በፋሸስቱ አብይ ቡድን በመላ አገሪቱ በተለያዩ የማጎሪያ ስፍራዎች በስቃይ የሚገኙትን የትግራይ ተወላጆች  በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

GSTS/ በዚሁ ደብዳቡው እንዳመለከተው  ፋሸስቱ የአብይ ቡድን ምንም ወንጀል ሳይኖራቸው በማንነታቸው ምክንያት በተለያዩ ማጎሪያ ስፍራዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እየተሰቃዩ ይገኛል፡፡

በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ስቃይ እንዲያበቃ  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የሰብአዊ መብት ተቋማት ችግሩን በሚገባ እንዲገነዘቡት ያሳሰበው GSTS

በተለይም በአፋር ሰመራ፡በምእራብ ትግራይና በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች  በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች  ከህግ አግባብ ውጭ ታስረው የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች በመሆናቸው  ዓለም አቀፍ ገለልተኛ ቡድን እንዲያጣራው ጠይቀዋል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በእስር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች  ድህንነታቸውን በተመለከተ  ሃላፊነት እንዲወስድ እና በተለይም ከምእራብ ትግራይና አብዓላ አከባቢዎች የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱና ንብረታቸውም እንደመለስላቸው GSTS በመግለጫው ጠይቋል፡፡

የሰብአዊ መብት ተቋማት  ቀደም ሲል የታሰሩና አሁን በመታሰር ላይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ድህንነታቸውን በተለመከተ እንዲከታተሉና ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቀው የGSTS መግለጫ   የትግራይ ተወላጆችን በማደን፤ በማፈንና በጅምላ በአዲስ መልክ የተቀሰቀሰው የብቀላ ወንጀል   የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮመሽንና  የዓለም ማህበረሰብ ጥረት እንዲያደርግም ጠይቀዋል፡፡

መብራህቱ ይባልህ

Previous articleየማህበራዊ ሚድያ ውሎ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች አቀባበል
Next articleፋሽስት አብይ በትግራይ ህዝቡ በረሃብ እንዲያልቅ አስቀድሞ በማቀድ የፈፀመው ተግባር ነው ስትል አክቲቪስት ምልእተ ገለፀች፤