Home ዜና ፋሽስት የአብይ ቡድን የትግራይ ህዝብ ለማጥፋት የመደበው ከፍተኛ ወታደራዊ  በጀት በአገሪቱ  ከፍተኛ ...

ፋሽስት የአብይ ቡድን የትግራይ ህዝብ ለማጥፋት የመደበው ከፍተኛ ወታደራዊ  በጀት በአገሪቱ  ከፍተኛ  የበጀት ቀውስ ማስከተሉ ተገለጸ፡፡

666
0

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የትግራይን ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የመደበው ከፍተኛ ወታደራዊ  በጀት   በአገሪቱ  ከፍተኛ  የበጀት ቀውስ   ማስከተሉን  ተገለጸ፡፡

ኳርቲዝ አፍሪካ የተባለ ድረ ገፅ እንደዘገበው ፋሽስት የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት ለማካሄድ ከአገር ውስጥ ባንኮች ብድር በመውሰድና ለካፒታል ፕሮጀክቶች  የተመደበው በጀት  ወደ ጦርነቱ በማዞር ለወታዳረዊ አገልግሎት ከፍተኛ ወጪ በማስወጣቱ  አሁን ላጋጠመው ሰፊ የበጀት ቀውስ ምክንያት ነው፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት ተከትሎ አለም አቀፍ አበዳሪዎችና የልማት አጋሮች ለኢትዮጵያ ይሰጡት የነበረው ብድርና ድጋፍ እንዲዘገይ በማድረጋቸው የአገሪቱ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መመናኑን ተከትሎ እና ለበጀት አመት ከተመደበው በጀት ውስጥ 25 በመቶውን ከውጭ ድጋፍና ከታክስ ይገኛል ተብሎ  ከታቀደው  እስከ አሁን ምንም አለመገኘቱና  ባለፉት ሁለት ወራት  ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶችም እዚህ ግባ የሚባል ገቢ አለመገኘቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡

በአገሪቱ አሁን የተፈጠረው ከፍተኛ  የወጪ በጀት ጉድለት የማያቋርጥ  የፋይናንስ ችግር ማስከተሉን የዘገበው  ድረ ገፁ ፋሽስቱ የአብይ ቡድኑ በትግራይ እያካሄደ ላለው የጄኖሳይድ ጦርነት አገልግሎት የሚውል ከፍተኛ የብር ኖት በማሳተሙ  ድጋሜ ከፍተኛ የአገር ውስጥ እዳ እንዲሸከም አድርጎታል ብሏል ዘገባው፡፡

ፋሽስቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 66 ቢሊዮን የብር ኖቶች ማሳተሙን ከፋሽስቱ ቡድን ፋይናንስ ሚኒስቴር ያገኘውን ምንጭ በመጥቀስ የዘገበው ኳርቲዝ የተባለ ድረ ገፅ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በበኩላቸው ችግሩ የብር ኖት ማሳተም ሳይሆን የብር ኖቱ ለምርታማነት ሳይሆን አለአግባብ እንዲውል በመደረጉ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

ፋሽስት የአብይ ቡድን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአገር ውስጥ ግምጃ ቤት 167 ቢሊዮን ብር መበደሩን ያመለከተው ዘገባው አሁን በድምሩ 1ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር የአገር ውስጥ እዳ እንዳለበት አመልክቷል፡፡

በዚሁ ምክንያትም ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የትግራይ ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የመደበው ለወታደራዊ አገልግሎት ያዋለው ከፍትኛ በጀት  አሁን በአገሪቱ  ከፍተኛ የዋጋ ንረትና የበጀት ቀውስ   ማስከተሉን  አስረድቷል፡፡

መብራህቱ ይባልህ

Previous articleAmnesty international በሁሉም ግፍ የተፈፀመባቸው አከባቢዎች ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀስ እንዲፈቀድለት ጠየቀ፡፡  
Next articleየትግራይና የአገው ህዝብ የዘመናት ታሪካዊና ማህበራዊ ግንኙነት ለመበጣጠስ የሚሞክሩ ሃይሎችን በጋራ መመከት እንደሚገባ ተገለፀ።