Home ዜና ፕሮፌሰር ቶኒ ማጋና በዶ/ር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ በጤና አጠበበቅ ዘርፍ ስኬት ሪፖርት...

ፕሮፌሰር ቶኒ ማጋና በዶ/ር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ በጤና አጠበበቅ ዘርፍ ስኬት ሪፖርት እጅግ ቅር መሰኘታቸውን ገለጹ::

558
0

የኖርዊጅያን ዩኒቨርስቲ የነርቭ ሳይቲስት የሆኑ ፕሮፌሰር ቶኒ ማጋና የፋሽስቱ የአብይ ቡድን የጤና ሚኒሰትር የሆነችው /ር ሊያ ታደሰ በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ አስመልክታ ምንም ሳትል ኢትዮጵያ በጤና አጠበበቅ ዘርፍ ስኬት ተቀዳጅታለች በማለት በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ ተገኝታ በሰጠችው ማብራሪያ እጅግ ቅር መሰኘታቸውን ገለጹ::

የኖርዌጃን ዩኒቨርስቲ የነርቭ ሳይቲስት የሆኑት ፕሮፌሰር ቶኒ ማጋና ለሃዋርድ ዩኒቨርስቲ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ፣ከ6 ሚሊዮን በላይ የትግራይ ሀዝብ በአሁኑ ወቅት የመድሃኒት፣ነዳጅና የኤሌክትሪክ መብራት አቅርቦት ፍጹም ተዘግቶበት ይገኛል ብሏል፣፣

የትግራይ ህዝብ በፋሽስቱ የአብይ ቡድንና በአምባገነኑ ኢሳያስ ቅጥር ወታደሮች ተቀናጅተው ባኖሩት ከበባና ክልከላ ምክንያት የመድሃኒት አቅርቦት እጅግ በሚያሳስብ ሁኔታ ላይ በሚገኝበት ባአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ዘርፍ ስኬት ማጉላት የማይገባ መሆኑን በደብዳቤያቸው አመላክተዋል::

በትግራይ ህዝብ ላይ እየሆነ ያለው ሁላችንም በእጅጉ የሚያሳስበን ነው ያሉት ፕሮፌሰር ቶኒ ማጋና፣ትግራይ ህዝብ አስከፊ ሁኔታና የመድሃኒት ክልከላው እያሳሰበን ባለበት ወቅት በአሜሪካ መልካም ታሪክ ያለው የሃዋርድ ዩኒቨርስቲ ክብሩ በማይመጥን መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት የጤና አገልግሎት ስኬትን ማጉላት ተገቢ አይደለም ብለዋል ፕሮፌሰሩ::

በትግራይ የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች የጤና ተቋማት የህክምና እና የጤና አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም ያሉት ፕሮፌሰር ማጋና፣እዛው በነበርኩበት ጊዜ እኔም የዓይን ምስክር ነኝ በማለት አብራርቷዋል::

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሚመሩት የጤና ሚኒስቴር ለትግራይ ሀዝብ የህክምና፣የመድሃኒት አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት በተገቢው መንገደ እንዳይሰጥ እንቅፋት ሲፈጥሩ እንደነበር እማኝ ነኝ ያሉት ሳይቲስቱ፣ሚኒስትሯዋ አንድ ጊዜ ወደ መቐለ ከተማ በተጓዙበት ወቅትም በመቐለ ዩኒቨርስቲ ምሁራንና በጤና ባለሙያዎች በትግራይ የጤና ዘርፍ ያሉ ችግሮችን እንዲወያዩ ተጋብዘው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርቷዋል፣ፈቶግራፍ ተነስተው ምንም ነገር ሳይሰሩ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል ብለዋል::

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ሰላማዊያን ዜጎች በፋሽስቱ የአብይ ቡድን የመድሃኒት አቅርቦት ክልከላ፣ በሰው ሰራሽ ረሃብ እንዲሁም በፋሽስቱ ቡድን እና በአምባገነኑ ኢሳያስ ቅጥረኛ ወታደሮች በፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት የጅምላ ግድያ ለሞት መዳረጋቸውን ገልጸዋል::

እንዲሁም በፋሽስቱ ቡድንና አምባገነኑ ወታደሮችበሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሴቶች ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን፣ሴቶቹ ታክመው የመዳን እድል እንዳይገጥማቸው እንኳን በመድሃኒት እጦት ለሞት ተዳርጓል::

ሆኖም ዶር ሊያ ታደሰ በትግራይን ህዝብ ላይ በደረሰው የጤና ችግር ምንም ሳይሉና ሆን ብሎው በመዝጋት በኢትዮጵያ ያለውን የጤና ስኬት ማውራታቸው አሳዛኝ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ፣ከውጪ ለጋሾች በእርዳታ የተገኙ መድሃኒቶች እንኳ በመንግስታቸው ቁጥጥር አልፈው ወደ ትግራይ እንደሚገቡ አስታውሷል፣፣ሚኒስትሯዋ ይህንን በዝምታ ተመልክተውታል::

አሜሪካን ጨምሮ ስድስት የአውሮፓ ሃገራት የፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ላይ ያደረሰው ክበባና ክልከላ በማንሳት የሰብአዊ ድጋፍ ያለገደብ እንዲገባ ጥሪ ማቅረባቸውን በማስታወስ፣ሚኒስትሯዋ ግን በጉዳዩ ምንም አለማለታቸው ገልጿል::

በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ከሆነችው አዲት የትግራይ ተወላጅ በሰልክ ተገናኝተው ማስራታቸውን በመግለጽ፣በዩኒቨርስቲው የፋሽስቱ ቡድን ያደረጃቸው ድብቅ ሰላዮች ፍራቻ ምክንያት በትግራይ ሀዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለመናገር እንዳልቻለች እና ድርጊቱ አሳዛኝ አጋጣሚ እንደሆነባቸው ገልጿል::   

አማረ ኢታይ

Previous articleየአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ብራድ ሼርማን   የፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው  ጄኖሳይድ የመሆን አቅም ያለው ወንጀል በተመለከተ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት  የተሟላ ግንዛቤ እንዳላቸው  አመለከቱ፡፡
Next articleየትግራይ መንግስት  ማእከላዊ ኮማንድ መግለጫ