Home ዜና Amnisti international and Human rights wotchs የጋራ ሪፖርትን በተመለከተ  የታዩ ህፀፆችን እንዲስተካከል...

Amnisti international and Human rights wotchs የጋራ ሪፖርትን በተመለከተ  የታዩ ህፀፆችን እንዲስተካከል  ተጠየቀ፡፡

949
0

በምእራብ ትግራይ ስለተፈፀሙ ዘግናኝ ግፎች  እ.ኤ አ April 20 2022 በጋራ ያወጡትን የጋራ ሪፖርትን በተመለከተ  የታዩ ህፀፆችን እንዲስተካከል ስለመጠየቅ በሚል አርእስት የትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ጥምረት፤ የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ማህበር፤ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ  የሰብአዊ መብቶች ማእከል እንዲሁም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የህግ መማክርት ማእከል በጋራ በፃፉት ደብዳቤ ለ Amnisti international ዋና  ጸሃፊ አግኔስ ካለማርድና ለ Human rights watchs ዋና ዳይሬክተር ኬኔዝ ሮዝን ጠይቀዋል፡፡

ማህበራቱ በዚሁ ደብዳቤቸው April 20 2022 “የትግራይ  ተወላጆችን ከዚሁ ምድረ ገፅ እናጠፋችኋለን በምእራብ ትግራይ በሰበአዊነት የተፈፀመ ወንጀል፤ የዘር ማፅዳት ወንጀል” በሚል ርእስ ስር ተቀነባበረ ሪፖረት እና ፊርማችን በዚሁ ደብዳቤ ስር ያስቀመጥን ማህበራት April 27 2022 ባካሄድነው ጉባኤ ሪፖርቱን ለመዳሰስ ሞክረናል ይላል ደብዳቤው ሲጀምር፡፡

ሪፖርቱ ከሚመለከታቸው የሰብአዊ መብቶች፣ አለምአቀፍ የጦርነት ህግና የፖለቲካ ሳይንስ የተለያየ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች በጥልቀት የመረመሩት ሪፖርት መሆኑን ያመለከተው የማህበራቱ ደብዳቤ ሁለቱም እውቅ የሰብአዊ መብት ተመጓች ድርጅቶች ፋሸስቱ የአብይ ቡድን፤ የአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖ እንዲሁም አምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት በምእራብ ትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀሙት አለም-አቀፍ የወንጀል ግፎች ለአለም ማጋለጣቸው ማህበራቱ አድናቆትን ችሮዋቸዋል፡፡ ትግራይን በመላና ምእራብ ትግራን ደግሞ በተለይ በሁለንተናዊ ከበባ ስር እንዲወድቁ በማድረግ የተፈፀሙ ግፎች ከአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ከሰብአዊ መብት ተማጓቾች እይታ ለመደበቅ የተደረገው ጥረት ሲታይ የሪፖርቱ  ፋይዳ ይበልጥ    የጎላ እንደሚያደርገው  የማህበራቱ ደብዳቤ ያስገነዝባል፡፡

 ሪፖርቱ በቀጣይ በምእራብ ትግራይ በተፈጸሙ  ዘርፈ ብዙና ሰፊ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ረገጣዎችና የአለም-አቀፍ የጦርነት ድንጋጌዎች ጥሰቶች ላይ  ገለልተኛ፣ ጥልቅና አጠቃላይ ምርመራ ለማካሄድ   የሚደረገውን ጥረት አስተዋፅኦ አንደሚኖረው የማህበራቱ እምነት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ማህበራቱ ሪፖርቱን በገመገሙበት ጉባኤ  በሪፖረቱ መስተካከል ያለባቸው አንዳንድ ግድፈቶች  ማሰተዋላቸውን የገለፀው ድብዳቤው በጦርነቱ ለተፈፀሙ ግፎች መነሻ ምክንያቶችና የጦርነቱን አውድ ባግባቡ ለመረዳት ካለው ጠቀሜታ አንፃር በሪፖርቱ የተካተቱ አሳሳቢ ጉዳዮችን መታረም እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡ የማይካድራው ጭፍጨፋ   በፋሸስቱ የአብይ ቡድንና ወገንተኛው የፋሽስቱ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩት  መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጋራ ሪፖርት  የተዛባ ትርክት ተፅእኖ  ስር  መውደቁ አግባብነት የለውም ብሏል፤ የማህበራቱ ደብዳቤ ምንም እንኳን  ለዚሁ  የተዛባ ትርክት ምሰሶ የሆኑት መሰረታዊ ጉዳዮች  በሁለቱም የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች የኋለ ኋላ ሀቁ   ፍርጥርጡ ቢወጣም ፋሸስቱ የአብይ ቡድን በትርክቱ የማይካድራው ጭፍጨፋ በትግራይ ተወላጆች እንደተፈፀመ እየተጠቀመበት እንደሆነ ደብዳቤው አብራርቷል፡፡ የማይካድረው ጭፍጨፋ የትግራይ ሃይሎች አካባቢውን ለቀው ከወጡ በኋላ የተፈፀመ  ግፍ በመሆኑ የትግራይ ሃይሎች ግፋን ለመፈፀም ፍላጎቱ ነበራቸው ቢባልም እንኳን  በማናቸውም ሁኔታ ከማካድራው ጭፍጨ በፊትም ሆነ በኋላ ግፉን ለመፈፀም ችለዋል የሚያስብል አመክንዮ የለም ብሏል፡፡

በሪፖርቱ ወንጀሉ የተፈፀመበት አካባቢ በትክክል  ምእራብ ትግራይ ተብሎ የተጠቀሰ ቢሆንም በአንዳንድ  ቦታ የሚከራክር  ቦታ ተብሎ በሪፖርቱ መጠቀሱ ሊታረም ይገባዋል ብሏል፡፡

በአምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት የተፈፀሙ ግፎች ባግባቡ አልተሰነደም ላለው ደብዳቤውም  ለአምባገነኑ የኢሳያስ ቡድን የተሳሰተ መልእክት እንዳያስተለልፍ መታረም እንደሚኖርበት  የማህበራቱ ደብዳቤ  አሳስቧል፡፡

Previous articleየኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ምስራቅ እዝ በፋሽስቱ ቡድን ሀይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
Next articleዘንድሮ አለም-አቀፍ የኮምኒኬሽን ቀን እንደማመጥ በሚል መሪ ሃሳብ ሲከበር የትግራይ ህዝብ ሰቆቃና መከራ መደመጥ አለበት ተብሏል፡፡