Home ዜና ‘Escaping Eritrea’ የተሰኘ  በፍሮንትላይን የቀረበው ዶክመንታሪ ፊልም የፒቦድይ አዋርድ አሸናፊ ሆነ፡፡

‘Escaping Eritrea’ የተሰኘ  በፍሮንትላይን የቀረበው ዶክመንታሪ ፊልም የፒቦድይ አዋርድ አሸናፊ ሆነ፡፡

517
0

የአምባገነኑ ኢሳያስ በኤርትራ ዜጎች ስለፈፀመው እና አሁንም እየቀጠለበት ስላለው አስደንጋጭ ግፍ አስመልክቶ በከፍተኛ ጥናት እና ምርምር የተዘጋጀው Escaping Eritrea የተሰኘ በፍሮንትላይን የቀረበው ዶክመንታሪ ፊልም  የፒቦድይ አዋርድ አሸናፊ ሆነ።

የኤርትራ ዜጎች ሃገራቸውን  ጥለው የሚሰደዱበት እና የሚሸሹበት ዋናው ምክንያት ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጠው በከፍተኛ ምርመራ ተሰንዶ በኢቫን ዊልያምስ ዳሬክተርነት የተዘጋጀው ስኬፒንግ ኤርትራ የተሰኘ የፍሮንትላይን ዶክመንተሪ ፊልም የፒቦድይ አዋርድ አሸናፊ ሆኗል። ፒቦይድ  አዋርድ በቴሌቬዠን፣ በራዲዮ በዲጂታል ሜዲያ እና በመሳሰሉ መንገዶች  የሚቀርቡ ዘጋቢ ፊልሞችን  ለአድማጭ ተመልካች የሚያቀርብ ተቋም ነው።

ፍሮንትላይንን ተሸላሚ ያደረገው ይህ ስኬፒንግ ኤርትራ የተሰኘው ዶክሜንተሪ በምድር ካሉ ሃገራት መካከል ሲኦልና ዜጎቻቸውን በሃይለኛ ቁጥጥር ከሚያስተዳድሩ ሃገራት መካከል ኤርትራ አንዷ ስለመሆንዋ ይተርካል።

ይህ ዶክመንታሪ ሲሰራ የኤርትራ ስደተኞችን እንደ ምንጭ በመጠቀም  የአይን እማኞችን ጋር ቆይታ በማድረግ ለመገመት የሚከብደው በኤርትራ ያለው ምድራዊ ገሃንም ለታዳሚ  በማድረስ ስለ አምባገነኑ ኢሳያስ  ትክክለኛ ማንንት ያጋለጠ ስራ  መሆኑ ነው ፍሮንትላይን ስለዚህ ዶክመንተሪ ሲገልፅ በዘገባው ያሰፈረው።

 በኤርትራ ስለሚገኘው ጨቋኙና አምባገነናዊ  ስርዓት የሚያጋልጠው ይህ ዶክመንተሪ  አምባገነኑ የኢሳያስ ቡድን በሃገሪቱ በርካታ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ የሚያሰቃዩባቸው አስደንጋጭ እስርቤቶች እንዳሉት እንዲሁም  ዜጎች በግዴታ ገደብ የለሽ  የባርነት  ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚገደዱም ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ፎንትላይን ያስረዳል።

ፒቦድይ አዋርድ ይህንን ዶክምንተሪ አሸናፊ ያደረገበት ዋና ምክንያት ብሎ እንደገለፀው ፍሮንትላይን ሚስጥራዊው እና በደንብ ያልተነገረለት እንዲሁም  የተደበቀው  የኤርትራ ሚስጥር በፊልም ቁልጭ አድርጎ ለማሳየት በመቻሉ ነው።  የኤርትራ ዜጎችን ለስደት እና ለስቃይ  የዳረገው አምባገነኑ ኢሳያስ  በዚህ ሰይጣናዊ ድርጊቱ ምክንያት ኤርትራን የአፍሪካ ሰሜን ኮርያ አሰኝቷታል ተብሏል በዘገባው።

ዶክመንታሪው አሁን ስላለው የአምባገነኑ ኢሳያሰ ቡድንን  ማንነት በደንብ የሚያሳይ ስለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን በኤርትራ ስደተኞች እና  በአፍሪካ ቀንድ እያጋጠመ ስላለው ቀውስ ማሳያ ሊሆን የሚችል ዘጋቢ ፊልም ስለመሆኑም ተነግሮለታል።

ፍሮንትላይን  በዚህ ዓመት የፒ ቦዲ አዋርድ አሸናፊ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከስኬፒንግ ኤርትራ  ፊልም በተጨማሪ ከዚህ በፊት በፊልፒንስ ስላለው የሚድያ ነፃነት አስመልክቶ የሰራው ታውዘንድ ካትስ በተሰኘው ዶክመንታሪም አሸናፊነት መጎናፀፉ ይታወሳል።

በታሪክ ፍስሃ 

Previous articleፋሽስቱ የአብይ ቡድን አገሪቷን ወደ ጦርነት በማስገባቱ የአገሪቱ ብር የመግዛት አቅምም በ26% ወርዷል ተባለ፡፡
Next articleአሜሪካ ለኤርትራ ህዝብ የሰብአዊ ድጋፍ እንዳትሰጥ በአምባገነኑ ኢሳያስ አገዛዝ መከልከልዋን አስታወቀች፡፡