Home ዜና የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ የፋሽስቱ ቡድን ሰላሙን ጥረት ከሚያደናቅፉ...

የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ የፋሽስቱ ቡድን ሰላሙን ጥረት ከሚያደናቅፉ ተግባራት መቆጠብ እንዳለበት አሳሰቡ።

2000

——

የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ይፋ የዳረገው የሰላም ፍላጎት ከልቡ ከሆነ ከአቋሙ ጋር የሚጣጣም ተግባር እና የሰላሙን ጥረት ከሚያደናቅፉ ተግባራት መቆጠብ እንዳለበት አሳሰቡ።

አቶ ጌታቸው የሰላም ሂደቱ የማይፈልጉት ተስፋፊው የአማራ ሃይሎች እና አምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚያደርጉት ጥረት ማምከን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እየቀጠለ ያለው ሰቆቃ እንዲያበቃ መሰራት እንደሚገባም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል አቶ ጌታቸው ረዳ ተስፋፊው የአማራ ሃይል ተጨማሪ ስግብግብ ፍላጎቱን ለሟሟላት ከሱዳን ጋር የለኮሰው ጦርነት በሃገሪቱ የተጀመረው የሰላም ጭላንጭል መልሶ የሚያጠፋ መሆኑን አስገነዘቡ።