የአውሮፓ ህብረት ክራይስስ ማናጅመንት ኮሚሽንና ሌሎች 15 የህብረቱ ሉኡኳን በመቐለ ከተማ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል።
—-
የአውሮፓ ህብረት ክራይስስ ማናጅመንት ኮምሽን እና የህብረቱ ልኡካን ከትግራይ አልፎ ለዓፋር እና ለ አማራ ህዝቦችም ሳይቀር አገልግሎት ይሰጥ የነበረው በትግራይ ትልቁ የጤና ተቋም የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ወደ ማይችልበት ደረጃ መድረሱን ተመልክተዋል።
በትልቁ የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ህንፃ ስር የሚሰማው ሰቆቃ ስቃይ አና ሰቀቀን በዓይናቸው የተመለከቱ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ከፊታቸው የሚነበበው ሀዘን የችግሩ ጥልቀት በአካል በማረጋገጣቸው የፈጠረባቸው ስሜት ከፊታቸውን ይነበባል።
ዛሬ መቐለ ተገኝተው ከትግራይ መንግስት እና ከትግራይ የሀይማኖት አባቶች የመከሩት የአውሮፓ ህብረት ሉኡካኑ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የነዳጅ እጥረት እና ሌሎች መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች መቋረጣቸው የፈጠረው ጫና መገምገማቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ልኡኳኑ ከትግራይ የሃይማኖት መሪዎች በነበራቸው ቆይታ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመው አና እየቀጠለ ያለው ወንጀል ጀኖሳይድ መሆኑ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን በስሙ እንዲጠሩት የሃይማኖት መሪዎቹ ማስገንዘባቸው ታውቋል።
የአውሮፓ ህብረት ልኡካኑ በትግራይ ሁሉም መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ማለትም የባንክ የስልክ የመብራት እና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲከፈቱ ጫና እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
የትግራይ ግብርናና ገጠር ልምት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገቦ ልኡካኑ ተደጋጋሚ በሪፖርት የደረሳቸውን ሀቅ አሁን ላይ በዓይናቸው ማረጋገጣቸው ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ሄለን ወልደሃንስ