Home ዜና ፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድንና ተስፋፊዉ የአማራ ሃይል የአገዉ ህዝብ በርሃብ አለንጋ ተስቃይቶ...

ፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድንና ተስፋፊዉ የአማራ ሃይል የአገዉ ህዝብ በርሃብ አለንጋ ተስቃይቶ እንዲሞት እያደረጉ መሆኑን የአብርገለ ወረዳ ኒራቕ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

1110

—-

ፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድንና ተስፋፊዉ የአማራ ሃይል በአገዉ ህዝብ ላይ እየፈፀሙት ባለው ግፍና በደል ህዝቡ በሰዉ ሰራሽ ርሃብ  እንዲያልቅ ማድረግ ይገኝበታል፡፡

የአብርገለ ወረዳ ኒራቕ ከተማ ነዋሪዎችም  ፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድንና ተስፋፊዉ የአማራ ሃይል የአገዉ ህዝብ በርሃብ አለንጋ ተስቃይቶ እንዲሞት ፈርደዉበታል ይላሉ፡፡

የትግራይና የአገው ህዝብን ለማለያየት በርካታ ፕሮፐጋንዳ ቢሰራጭም ሳይሳካ በመቅረቱ አሁንም የአገው ህዝብን ለማንበርከክ ያለመ በርካታ ግፍ እየተፈፀመ መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

የትግራይ መንግስት በተለያዩ ግዝያት ሰለ ሰላም እየሰበከ እንደመጣ ያስታወሱት ነዋሪዎቹ  አሁንም የአለም ማህበረሰብ የትግራይና የአገዉ ህዝብ ያለበትን ችግር ተረድቶ መፍትሄ እንዲያመጣና  የተስፋፊው የአማራ ሃይሎች እና ሊሂቃኖች እየፈፀሙት ካሉት አስነዋሪ ድርጊታቸዉ ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል፡፡

በፍረወይኒ መንገሻ