Home ዜና በደቡብ ሱዳን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን  በተዘጋጀዉ መድረክ   ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ማንነት...

በደቡብ ሱዳን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን  በተዘጋጀዉ መድረክ   ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ማንነት መሰረት ያደረግ ግፍ ተጋለጠ፡፡

787
0

በደቡብ ሱዳን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን  በተዘጋጀዉ መድረክ   ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ማንነት መሰረት ያደረግ ግፍ ተጋለጠ፡፡

——   

አንዲት ትግራወይቲ አንስት ዓለምአቀፍ ስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ በደቡብ ሱዳን ጁባ በተዘጋጀዉ መድረክ በደቡብ ሱዳን የፋሽስቱ ቡድን አምባሳደርን አጋለጠች፡፡

በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ ጀኖሳይድ በመጋለጡ አምባሳደሩ ህፍረት ተከናነቦ እንደፈረጠጠም ምንጮች ዘግበዋል፡፡

ቅዱሳን አረጋዊ ትባላለች በደቡብ ሱዳን በተለያዩ የስራ መሰኮች ላይ ተሰማርታ ትገኛለች፡፡ በትግራይ በታወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት ከአገሯ ተሰዳ በደቡብ ሱዳን መጠለያ ጠይቃ እየኖረች ያለችዉን ቅዱሳን  አለም አቀፉ የስደተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ በደቡብ ሱዳን ጁባ የሚገኘዉ የተባበሩት መንግስት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ቅርንጫፍ በተዘጋጀዉ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ኢትዮጵያ በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀመች ያለችዉን ወንጀል አጋልጣለች፡፡

ቅዱሳን አረጋዊ  ኢትዮጵያ በትግራይ እየፈፀመች ያለችዉን  ጀኖሳይደ በማጋለጧ ተከትሎ በበዓሉ  የክብር  እንግዳ ሆኖ የታደመዉ  በደቡብ ሱዳን የፋሽስቱ አብይ ቡድን  ዲፕሎማት  ናቢል ናህዲ   ሃፍረቱን ተከናንቦ ከመድረኩ እንዲወጣ  ሆኗል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ተወላጆች ላይ እየፈፀመ ያለዉን ማንነት መሰረት ያደረግ ግፍ  የተረዳችዉ ቅዱሳን በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችና በደቡብ ሱዳን የትግራይ ተወላጅ  የሰላም አሰከባሪ  አባላት ሁኔታዉ በደንብ እንዲረዱትና  ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዉ የስርዓቱ ግፍ ገፈት ቀማሽ እንዳይሆኑ ባደረገችዉ ጥረት ብዙ የትግራይ ተወላጆች በደቡብ ሱዳን መጠለያ እንደጠየቁ የገለፀች ሲሆን በዚህም በፋሽስቱ ቡድን ተላላኪዎች ዓይን ውስጥ መግባቷን  ትገልፃለች፡፡

ቅዱሳን አረጋዊ  ከጎደኞቿ ጋር በመሆን ከደቡበ ሱዳን ጋር ባደረጉት የመግባባት ስራ  ከአራት ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች  ጥገኝነት እንዲያገኙ የበኩልዋን ሚና ተጫውታለች ተብሏል፡፡

በደቡብ ሱዳን የፋሽስቱ አብይ ቡድን አምባሳደር  ነቢል መሃዲ በነበረበት መድረክ በሰጠችው ምስክርነት አምባሳደሩ በፋሽስቱ ተግባራት የተሸማቀቀ ሲሆን  መድረኩን አቋርጦት መሄዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በደቡብ ሱዳን የፋሽስቱ ቡድን አምባሳደር ወጣትዋ በህገ ወጥ ስራዎች የተሰማራች በመሆንዋ የደቡብ ሱዳን መንግስት ወደ አገርዋ ሊያባርራት ይገባል በማለት የሃሰት  ውንጀላ ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ

Previous articleእንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የአለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል ለአፍሪካ ቀንድ ቀይ ባህር አካባቢ ልዩ መልእክተኛ ሾመች።
Next article34ኛው የትግራይ ዝክረ ሰማእታት ቀን በጨርጨር ነዋሪዎች ከትግራይ ሰራዊት ጋር በመሆን  ሰማእታትን በሚዘክሩ ሁነቶች  ተከብሮ ውሏል፡፡