Home ዜና የኢሳያስ ወታደሮች በትግራይ ጀኖሳይድ ጦርነት ውስጥ  መሳተፋቸው  የተባበሩት መንግስታት  የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ  ...

የኢሳያስ ወታደሮች በትግራይ ጀኖሳይድ ጦርነት ውስጥ  መሳተፋቸው  የተባበሩት መንግስታት  የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ     አረጋገጠ ፡፡

1252
0

የኢሳያስ ወታደሮች በትግራይ ጀኖሳይድ ጦርነት ውስጥ  መሳተፋቸው  የተባበሩት መንግስታት  የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ     አረጋገጠ ፡፡

—–

በሺዎች የሚቆጠሩ የአምባገነኑ የኢሳያስ ቅጥረኛ ወታደሮች  በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የጀኖሳይድ ጦርነት ውስጥ  መሳተፋቸውን  የተባበሩት መንግስታት  የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ   ልዩ መርማሪ   አረጋገጡ ፡፡

አምባገነኑ ኢሳያስ  ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ታዳጊዎችን  ለውትድርና  አስገድዶ  እየመለመለና   በትግራይ የስደተኞች መጠለያ   የነበሩ ስደተኞችን  በሀይል በመውሰድ ግፍ እንደፈፀመባቸው ገልጿል ፡፡

ከሁለት ሳምንታት በፊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት   በሁሉም አገሮች  በተለይ ደግሞ  የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ይካሄድባቸዋል ብሎ ያሰባቸውን አገራት  ያለውን  የሰብአዊ መብት ሁኔታ ምን ይመስላል  በሚል የተደረገ ጥናት ለውይይት  ቀርቧል ፡፡

በቀረበው ጥናት ኤርትራ በአለማችን በሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚፈፅሙ አገራት ተርታ ውስጥ እንደምትገኝና   ምንም  መሻሻል ያልታየባት አገር እንደሆነች አሁንም ወደ  ባሰ ሰብአዊ ቀውስ መሸጋገርዋን  ይገልፃል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የሰብአዊ መብት ምክር-ቤት በሰብአዊ መብት የኤርትራ ልዩ  መርማሪ /  የሆኑት መሀመድ  ዓብዲሰለም ባቢካርካ, በሺዎች የሚቆጠሩ የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት      በትግራይ ህዝብ  የ ጀኖሳይድ  ጦርነት  በመሳተፍ   በትግራይ ህዝብ ላይ ብዙ ግፍ  ማድረሳቸውን  መስክረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት  ምክር-ቤት  ኤርትራ   ህፃናትን   ለውትድርና  መመልመሏ   በትግራይ በተካሄደው ጦርነትም  መሳተፋቸው   በማስረጃ  መረጋገጡ  አስረድተዋል፡፡

ከዘህ በተጨማሪ   የአምባገነኑ ወታደሮች  በትግራይ ከሚገኙ የኤርትራ መጠልያ ካምፖች   ሕፃፅ እና ሽመልባ  ተፈናቃዮች አፍኖ እንደወሰደ እና  በተፈናቀዮቹ ላይ የእስር እና የተለያዩ ቅጣት እንደወሰደባቸው   እና በሀይልም ወደ ውትድርና እንዳስገባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  ልዩ መርማሪ አብራርተዋል ፡፡

መአዲ ሀይለ

Previous articleየኢሳያስ ወታደሮች በትግራይ ጀኖሳይድ ጦርነት ውስጥ  መሳተፋቸው  የተባበሩት መንግስታት  የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ     አረጋገጠ ፡፡
Next articleእንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የአለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል ለአፍሪካ ቀንድ ቀይ ባህር አካባቢ ልዩ መልእክተኛ ሾመች።