Home ዜና ለትግራይ ዳግም ግንባታ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና

ለትግራይ ዳግም ግንባታ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና

362

በትግራይ ዳግም ግንባታ የንግዱ ማህበረሰብ ኣስፈላጊነት በሚል ርእስ 22 የኢትዮጵያ የንግድ ተቋማትና የባንኮች የስራ ሓላፊዎች በተገኙበት የትግራይ ዳግም ግንባታ ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ የግል የንግድ ድርጅቶች ሚና ምን መሆን ኣለበት በሚል በኣዲስ ኣበባ ውይይት እየተካሄደ ይገኛልⵆ

በውይይቱ የትገኙት የትግራይ ግዚያዊ ኣስትዳደር ፕሬዝዳንት ኣቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ህዝብ ሃብት በታቀደ ሁኔታ በተለይም በኤርትራ ሰራዊት እንዳይመለስ ተደርጎ መውደሙን ኣስገንዝበዋልⵆበመሆኑም እነዚህን የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ረገድ የግል ባለሃብቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲፈፅሙ ኣቶ ጌታቸው ጥሪ ኣቅርበዋል።

የትግራይ የንግድ ማሕበራት ቻምበር ፕሬዝዳንት ኣቶ ኣሰፋ በበኩላቸው የትግራይ ኢንቨስትመንትና ንግድ ተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ በባንኮች ብድርን የማቅረብ ችግር ለዳግም ግንባታው ፈታኝ እንድሚያደርገው ተናግረዋል። በትግራይ ተቋማትን ወደ ስራ ለማስገባት የኢትዮጵያ የንግድ ተቋማትና የፌደራል መንግስት ኣጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ ኣቅርበዋል።

የኣፍሪካ ቢዝነስ ፎር ፌለውሽፕ ኢኒሸቲቭ ተወካይ ወ/ሮ ዳለያ ኣሸናፊ ደግሞ የትግራይ ቱሪዝምና ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ኮንፈረንስ ለማካሄድ መታቀዱንና የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።በተጨማሪም ከብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ጋር በመሆን በጦርነት ተሳታፊ የነበሩ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።