Home ዜና ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም ህዝብን ለችግርና ለእልቂት የሚዳርጉ አገራትን መሪዎች ተጠያቂ ...

ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም ህዝብን ለችግርና ለእልቂት የሚዳርጉ አገራትን መሪዎች ተጠያቂ  እንዲሆኑ   በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት ፀደቀ፡፡

940

ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም ህዝብን ለችግርና ለእልቂት የሚዳርጉ አገራትን የሚወቅስና  በዚህ ድርጊት ፋሽስቱ አብይን ጨምሮ የሚሳተፉትን መሪዎች ተጠያቂ  እንዲሆኑ የሚያስችል ውሳኔ በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት በሙሉ ድምፅ ፀደቀ፡፡

የአሜሪካ የእርዳታ እህልን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም በህዝባቸው ላይ የረሃብ ቸነፈር እንዲፈጠር የሚያድርጉ አገራት የሚጠየቁበት አሰራር ባለመኖሩ በርካታ የአለም ህዝቦች ለእልቂት እየተዳረጉ መሆናቸው መነሻ በማድረግ ውሳኔው በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት በሁለቱ ፓርቲዎች የጋራ ስምምነት መጽደቁ ነው ፎሬን ሪለሽን የተሰኘ ድረ ገፅ የዘገበው፡፡

ባለፈው ግንቦት ወር  የህግ መወሰኛ ምክር-ቤቱ  የሁለቱም ፓርቲዎች የም/ቤቱ አባላት  ያረቀቁትና  አሁን ደግሞ ይሁንታ ያገኘው ይህንኑ ውሳኔ ወር ባልሞላው ጊዜ ወዲያውኑ  በህግ መወሰኛ ም/ቤቱ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት የፀደቀው ይህ ውሳኔ በአለማችን ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም ህዝብን ለችግርና ለእልቂት የሚዳርጉ አገራት የሚጠየቁበት አሰራር እንዲኖር የሚያደርግ ህግ እንዲወጣ የጀመሩትንን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገ ነው ብሏል ድረገፁ፡፡

ከሩሲያና ከዩክሬን ጦርነት በተጨማሪ በትግራይ፤ በደቡብ ሱዳንና በየመን በተካሄዱትና በመካሄድ ላይ ባሉት ጦርነቶች ለህዝቡ ደንታ የሌላቸው አካላት ሆን ብለው የግብርና ግብአቶችና የመሰረተ ልማት አውታሮች  አስቀድመው እንዲወድሙ በማድረግ ህዝቡን ለከፋ ረሃብ ሲዳርጉት እየተስተዋለ መሆኑን ለአሁኑ ውሳኔ አንዱ ምክንያት መሆኑን ድረገፁ ዘግቧል፡፡

የመሰረተ ልማቶችን እንዲወድሙ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ገበያውን በራሳቸው ቁጥጥር ስር እንዲገባ በማድረግ ወደ ህዝቡ ሰብአዊ እርዳታ እንዳይገባ ከበባና ክልከላ በመፈፀም ህዝቡን  ለከፋ ረሃብና ችግር እየዳረጉት ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ብዙ ሰላማዊያን ሰዎች ለሞት እንዲዳረጉ በማድረግ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አላማቸውን ለማሳካት እንደ ጦር መሳሪያ  እየተጠቀሙባቸው በመሆኑ እነዚህ ስግብግቦች ከዚህ በላይ እንዲሄዱ ላለመፍቀድ ውሳኔ ማስተላለፉ ተገቢ መሆኑን የህግ መወሰኛ ም/ቤቱ ውሳኔን  ጠቅሶ ድረገፁ ዘግቧል፡፡

የህግ መወሰኛ ም/ቤቱ  ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ  ለሚጠቀሙ ፋሽስቱ አብይን ጨምሮ  ለሩሲያው ፕሬዚዳንትና የሌሎች አገሮች መሪዎችን  ግልፅ መልእክት እንዳለው ያመላከተ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት የሚያካሂዳቸው የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች ላልተፈለገ አላማ ለማዋል ለሚንቀሳቀሱ ሁሉ እድል የማይሰጣቸው ነው ብሏል፡፡

ከሴናተሮቹ መካከል ጂፍ መርክለይ  ከዩክሬን እስከ ሶሪያና ኢትዮጵያ ያሉ እጅግ አስፈሪዎችና ስግብግቦች የእርሻ መሳሪያዎችን እንዲወድሙ ከማድረግ በተጨማሪ ሰብአዊ እርዳታ ወደ ህዝቡ በወቅቱ እንዳይደርስ ማስተጓጎላቸውን መሰረታዊ ሸቀጦች ወደ ህዝቡ እንዳይዳረሱ ገበያውን ማዛባታቸው እንደ አብነት ጠቅሰዋል፡፡

የሴኔቱ አባላት ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ ሲያፀድቁ ለጥቃት እየተዳረገ ያለውና ምንም አይነት ጥፋት ካልፈፀመው ህዝብ ጎን የሚቆሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ለመጠቀም ለሚፈልጉ አገራት እድሉ የማይሰጣቸው መሆኑን ያመላክቷል ብለዋል ሴናተር መርክለይ፡፡

ሴናተር ኮሪ ቦከር  በበኩላቸው ምክር ቤቱ ያስተላለፈው ጠንካራ ውሳኔ በተለያዩ የአለም አገራት እየተካሄዱ ያሉትና እስካሁን እልባት ያላገኙት ጦርነቶች እንዲያበቁ  የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ የጦርነቱ ሰለባ እየሆኑ ያሉት በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰላማዊያን ሰዎች በአለም አቀፍ ደረጀውን የጠበቀ የምግብ አቅርቦት በወቅቱ እንዲያገኙ ያስችሏል ማለታቸውን  ድረገፁ ዘግቧል፡፡

ሴናተር ጆን ቶም  በበኩላቸው ረሃብና እርዛት በማንኛውም መልኩ ለጦር መሳሪያ መዋል የለበትም ካሉ በኃላ ውሳኔው የአሜሪካ መንግስትና አጋሮቹ በቅንጅት በመስራት ግለሰቦችና መንግስታት ጦርነትን በመቀስቀስና ረሃብን ለጦር መሳሪያ ሲያውሉ ተጠያቂነት እንዲኖራቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡      

  በተካ ጉጉሳ