Home ዜና በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ዝርፊያ እና የባንኮች ኃላፊነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡

በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ዝርፊያ እና የባንኮች ኃላፊነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡

1194

ከፍተኛ ዝርፊያ  ከሚካሄዱባቸው ባንኮች መካከል ቀዳሚው ንግድ ባንክ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክ እና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ በተከታይነት እንደሚገኙበት ነው የተገለፀው  በቼክ የሚፈጸሙ፣ በቁጠባ ሂሳብ ላይ፣ በሃዋላ በሚላክ ገንዘብ ላይ፣ የይለፍ ቃል  ማጭበርበር  ብሎም በሌሎች መንገዶች ስርቆቱ እንደሚፈጸም  ነው የተገለፀው፤

በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ምዝበራዎች በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 1.9 ቢሊዮን ብር ኪሳራ  ኣድርስዋል፡፡

አሳሳቢ የሆነው በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ዝርፊያ እና የባንኮች ኃላፊነት በሚል ርእስ  ቢቢሲ  አንድ ባለ ታሪክን  ዋቢ በማድረግ  ይዞት በወጣው ዘገባ፤ 

አቶ እንዳለ ገ/መድኅን ከሚሰሩበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት የቁጠባ አገልግሎት በብድር ያገኙትን  200 ሺህ ብር ለጋራ መኖሪያ ቤት ቅድሚያ ክፍያ ለመክፈል በማሰብ በባንኩ ሙሉ እምነት በመጣል  አስቀምጠው በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ የገለፀው የቢቢሲ  ዘገባ ነገር ግን “ከባንክ ነው የምንደውለው”በሚሉ  ያልታወቁ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያካሂደው “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብር ላይ የሞተር ሳይክል  ሽልማት እንደደረሳቸው መነገራቸውንና በዚህም የተለያዩ መረጃዎችን እንደተጠየቁ የገለፁት አቶ እንዳለ   በተጠየቁት መሰረት  ሁሉን እንደተናገሩና በመጨረሻም በአቢሲኒያ እና በንግድ ባንክ አካውንቶቻቸው ውስጥ የነበረው 195 ሺህ ብር እንደተወሰደባቸው  ለፖሊስ ያላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ ይዘው ቢያመለክቱም፣ እስካሁን የተያዘ ተጠርጣሪ  አለመኖሩ በሃገሪቱ ያለው የፍትህ ስርኣት አልበኝነትን ያመላክታል፡፡ 

እንደ ቢቢሲ ዘገባ  ይህ የአቶ እንዳለ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ኣሁን ላይ በርካታ ሰዎች እየገጠማቸው ያለ  የማጭበርበር ወንጀል ሲሆን ዝርፊያው በተለይም የሞባይል ባንኪንግ አገልገሎት የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ያነጣጠረና በርካቶች በተለያየ ማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ እሮሮ ሲያሰሙ የከረሙበትም ጉዳይ መሆኑ ኣስነብብዋል። በፋሽስቱ የሚመራው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ የማጭበርበር ድርጊት ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲሁም ክስ የተጀመረባቸው መዝገቦችን በተመለከተ አድርጊያለው ባለው ጥናት  በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ምዝበራዎች መበራከታቸውን የገለፀው ዘገባው የሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ በመዝገብ የተያዙት ወንጀሎች በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 1.9 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማድረሳቸውንም ነው ጥናቱ የሚጠቁመው።

በዝርዝሩም ከፍተኛ ዝርፊያ ያጋጠመው በንግድ ባንክ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክ እና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክም እንደሚገኙበት ነው የተገለፀው። በቼክ የሚፈጸሙ፣ በቁጠባ ሂሳብ ላይ፣ በሃዋላ በሚላክ ገንዘብ ላይ፣ የይለፍ ቃል  ማጭበርበር  ብሎም በሌሎች መንገዶች ስርቆቱ እንደሚፈጸም የተገለፀ ሲሆን በተለይም  በሞባይል ባንኪንግ የሚፈጸመው ስርቆት በርካታ ስልቶች ያሉትና  ከተዋናዮቹ መካከል የባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና ሌሎች የባንክ ሠራተኞች ጭምር እንደሚሳተፉበትም ቢቢሲ ይዞት በወጣው ዘገባ የገለፀው። የባንክ ቤቱ ሃላፊዎች ጨምሮ ሠራተኞቹ ከደንበኞች አካውንት ጋር የራሳቸውን ወይም የዘመዶቻቸውን ብሎም የጓደኞቻቸውን ቁጥር በማያያዝ እና ሐሰተኛ ቅጽ በመሙላት ስርቆቱ እንደሚፈፀም ነው   ዘገባው የገለፀው።

ፍሬሂወት ተ/መድህን