Home ዜና በተለያዩ አህጉር የሚገኙ የትግራይ ዲያስፖራዎች  ተቃዉሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

በተለያዩ አህጉር የሚገኙ የትግራይ ዲያስፖራዎች  ተቃዉሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

1091

በትግራይ ህዝብ ላይ ከአምስት መቶ  ቀናት በላይ ያስቆጠረዉ  ከበባና ክልከላ እንዲያበቃ አለም አቀፍ አካላት   ፍትህ እንዲሰጡ  የትግራይ ዲያስፖራ  ጥሪ አቀረቡ፡፡

የዲያስፖራው ማህበረ-ሰብ ለፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ለአምባገነኑ  ኢሳያስአፈወርቂ በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲና በለንደን ከተማዎች ትልቅ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

በአብይ ቡድን፣ በአምባገነኑ የኢሳያስ አፈወርቂ ቅጥረኛ ሰራዊትና ተስፋፊዉ የአማራ ሃይል በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀሙት ያሉት የጀኖሳይድ ጦርነት እንዲያቆሙ ተቃውማቸው አሰሙ፡፡ በመላዉ አለም የሚገኙ የዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ ትግላቸዉን አጠናክረዉ በመቀጠል፣ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለዉ ጀኖሳይድ፣ ከበባና ክልከላ እንዲያበቃ እንዲሁም እየደረሰ ያለዉ ርሃብና ሞት የአለም ማህበረ-ሰብ እንዲታደገው አሳስበዋል፡፡

በዚህም ዋሽንግተን ዲሲና አከባቢዋ የሚኖሩ የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ፅህፈት ቤት በመገኘት በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ ጀኖሳየድ ያቁም፣ ከበባዉና ክልከላዉ ይከፈት  ሰብአዊ እርዳታ ወደ ህዝቡ ይድረስ የሚሉ ፅህፎቸን በመያዝ  መፈክሮቻቸዉን በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

በተካሄደዉ ሰልፍ የትግራይ ዲያስፖራ ህፃናት የተሳተፉበትና በርከት ያሉ የትግራይ ተወላጆችና  የትግራይ ወዳጆች ተሳትፈዉበታል፤ በተመሳሳይ ፋሽሰቱ ቡድን ለመቃወም ከታላቋ #ቢሪታንያ የተሰባሰቡ የትግራይ ተወላጅ ዲያስፖራ በለንደን ከተማ የተቃዎሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

 የተካሄደዉ ሰልፍ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመዉ የጀኖሳይድ ጦርነት ከአምስት መቶ በላይ ቀናት እንዳስቆጠረና በትግራይ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለዉ ከበባና ክልከላ እንዲያቆሙ፣ ወራሪ ሃይሎች ከትግራይ መሬት ለቀዉ እንዲወጡና ሌሎች መፈክሮችን ያሰሙበት ሲሆን በታላቋ ቢሪታንያ የሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ የፋሽስቱ ቡድን የጀኖሳይድ ጦሩነቱ እስክያቆም ድረስ ትግላቸዉን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ