Home ዜና በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን የጀኖሳይድ ጦርነት እንዲያበቃ የአውሮፓ ህብረት ትኩረት ሰጥቶ...

በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን የጀኖሳይድ ጦርነት እንዲያበቃ የአውሮፓ ህብረት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በአፍሪካ ቀንድ  ልዩ መልእክተኛ   ገለፁ፡፡

1790

—-

ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን የጀኖሳይድ ጦርነት እንዲያበቃና ችግሩ በሰላማዊ ውይይት እንዲፈታ የአውሮፓ ህብረት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በአፍሪካ ቀንድ የህብረቱ ልዩ መልእክተኛ አኔት ዊበር ገለፁ፡፡

የትግራይ ህዝብ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኝና  በፋሽስቱ ቡዱን ከአንድ አመት በላይ የተቋረጡትን መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ዳግም አገልግሎት እንዲጀምሩ ህብረቱ እየሰራበት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ህብረቱ ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን የጆኖሳይድ ጦርነት የአለም ማህበረሰብ እንዲያውቀው ከማድረግ ጀምሮ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ያልተቆጠበ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ልዩ መልእክተኛዋ  በሰላም ድርድሩ ዙሪያ እንዲሁም በትግራይ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ዳግም አገልግሎት ስለሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ክትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት  ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ግፍ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በልዩ ሁኔታ እንዲያዩት ከማድረግ በተጨማሪ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ ለማድረግ የአውሮፖ ህብረት የሰብአዊ ቀውስ አመራር የሚገኙበት ቡዱን ወደ ትግራይ በመላክ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ በአካል ተገኝተው ተመልክተዋል፡፡

የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ደ/ር ደብረፅን ገ/ሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫ የሰላም ድርድሩን ለማካሄድ የተቋረጡ የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች መጀመር እንዳለባቸው ማሳሰባቸው ይታወቃል፡፡

ልዩ መልእክተኛዋ ከፋሽስቱ ቡዱን አመራሮች ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ወደ ትግራይ በመምጣትም ከትግራይ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት የሚያደርጉ መሆናቸው አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ጨምሮ በርካታ የአለም አገራት  አገሪቷ አጋጥሟት ያለውን ችግር በሰላማዊ ውይይት እንዲፈታ ጥረት እያደረጉ ሲሆን የፋሽስቱ ቡዱን ግን ወደ ድርድሩ ላለመግባት የተለያዩ ምክንያቶች በመፍጠር የማደናቀፍ ተግባር እያካሄደ ይገኛል፡፡

የትግራይ መንግስት ግን በአገሪቷ ያጋጠመው የፖለቲካዊ ችግር የፈጠረው በመሆኑ መፍትሄው ውይይት በማድረግ ብቻ የሚፈታ መሆኑን ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ ለአለም ማህበረሰብ ሲያስታውቅ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

እንዲሁም ለሰላማዊ ውይይቱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል የፋሽስቱ ወታደሮች በማሸነፍ በጊዜያዊነት ተቆጣጥሮአቸው ከነበሩት ከአዲስ አበባ ደጃፍና ከተለያዩ የአማራና የዓፋር አካባቢዎች በመልቀቅ ሰራዊቱን ወደ ትግራይ አዋሳኝ ከተመለሰ ከስድስት ወራት በላይ ማሰቆጠሩ ይታወሳል፡፡

ተካ ጉግሳ