Ap ምእራብ ትግራይን ሳይጨምር አንድ የተደረገን የዳሰሳ ጥናት ዋቢ አድርጎ እነደዘገበው ከሰኔ 2013 አስከ መጋቢት 2014ዓ.ም በተመጣጠነ የምግብ ዕጥረት ምክንያት የሞቱት የትግራይ ህፃናት ቁጥር ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ሊጨምር ይችላል፡፡ ምክንቱን ሲያስቀምጥ ወላጆች በትራንስፖርት እጥረት ቸግር ሳቢያ ልጆቻቸውን ወደ ጤና ተቋማት ለማምጣት ያልቻሉ ብዙ ናቸውና ብሏል፡፡
የዜና አውታሩ አንድ ሃኪምን ጠቅሶ እንደዘገበው እንቅስቃሴያችን በእጅጉ የተገደበ በመሆኑና የሆነውን ሁሉ ለማወቅ አልቻልንም በጤና ተቋማት በምግብ እጥረት ሳቢያ የሞቱት ህፃናት ቁጥር ማግኘት የቻልነው ቁጥር ግን ይሄው ብቻ ነው፡፡ 115 ሺህ በላይ በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ክፉኛ የተጎዱት የትግራይ ህፃናትን ጨምሮ ከ90 በመቶ የትግራይ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚስፈልገው ያመለከተው የአሶሽዬትድ ፕሬስ ዘገባ የመንግስት ሰራተኞች ለአስር አስራ አንድ ወራት ወርሃዊ ደመወዛቸውን ባለማግኘታቸው ለልጆቻቸውን ቀለብ ለመግዛት እንዳልቻሉና ከተሜው የሚያመርትበት የእርሻ ቦታ ስለሌለው በከተማ በተመጣጠነ የምግብ እጥረት የሚሰቃዩ ህጻናት የበረታ እንደሆነ አስረድቷል ዘገባው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መረጃ መሰረት በማድረግ ሰብአዊ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት ወደ 700 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ለቸነፈር መሳይ ችግር መጋለጡንም ዘገባው ያስረዳል፡፡ አንድ ወር ሊሆነው ከተቃረበው የግጭት ማቆም ውሳኔ ከምንም ይሻላል ለማለት ካልሆነ በስተቀር ወደ ትግራይ የተጓጓዙት የእርዳታ እህል የጫኑ ተሸከርካሪዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው ብሎ አንድ በቅርቡ ትግራይን የጎበኘ የእርዳታ ለጋሽ ድርጅት ሰራተኛ እንደገለፀለት Ap በዘገባው አመላክቷል፡፡ ትናንት በናይሮቢ ኬንያ በተካሄደ ስብሰባ የተሳተፈው ይሄው የእርዳታ ለጋሽ ድርጅቱ ሰራተኛ በተጨማሪ ያለውን ችግር ለመቅረፍ በሳምንት 2ሺ የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ማምራት ይኖርባቸዋል ማለቱ ተዘግቧል፡፡