——
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ በፈጠረዉ ከበባና ክልከላ በትግራይ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት የንዋያተ ቅዱሳን መገልገያ እጥረት እንዳጋጠማቸዉ የትግራይ ሃገረ ስብከት አስታወቀ፡፡
ወደ ትግራይ ለአብያተ-ክርስትያናት የሚያገለግሉ ምንም ዓይነት ንዋያተ ቅዱሳት መግባት በማቆማቸዉ ህዝባቸዉን ለማገልገል እንደተቸገሩም ተገልፆል፡፡
ሃምሌ 11 ቀን 2014 ዓ/ም ከመላዉ ትግራይ የተዉጣጡ ሊቃዉንት ና ከሃገረ ስብከቱ የተወከሉ የሃይማኖት አባቶች በትግራይ አብያተ ክርስትያናት ስላለዉ ችግር ዙርያ ተወያይተዋል፡፡
በዉይይት መድረኩ የተገኙት ከመላዉ ትግራይ የተዉጣጡ የሃይማኖት መሪዎች በትግራይ በተፈጠረዉ ከበባና ክልከላ ምክንያት በትግራይ የሃይማኖት አስተምህሮ ለመስጠት አዳጋች እንደሆነና ከጦርነቱ የተረፈዉን የትግራይ ህዝብ በአራቱ ማእዘን በመዘጋቱ፣ የሃይማኖት ስርዓት አገልግሎት እየተናጋበት እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ያለፉት ስምንት ወራት በትግራይ ብዙ ሰዉ ሙቶል ንብረትም ወድሟል፤ እንዲሁም ከርሃቡና ከበሽታዉ በዘለለ ለአብያተ-ክርስትያናት የሚያገለግሉ ንዋያተ ቅዱሳት ሁለት ዓመት ሙሉ ወደ ትግራይ ባለመግባቱ እጥረት እንዳጋጠማቸዉና ህብረተ-ሰቡን ማገልገል እንዳልቻሉ የትግራይ የኦርተዶክስ የሃይማኖት አባቶች ተናገሩ ፡፡
በትግራይ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት በተለያዩ ግዝያት ስለ ሰላም አስፈላጊነት ሲሰብኩ የመጡ ሲሆን አሁንም የትግራይ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሁሉም ነገር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በከበባዉና በክልከላዉ ምክንያት በትግራይ አብያተ ክርስትያናት ሃይማኖታዊ ትምህርት ለመስጠት አዳጋች ሁኖል ያሉት የሃይማኖት አባቶቹ ችግሩ እንዲፈታ የአለም ማህበረ-ሰብ የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በፍረወይኒ መንገሻ