Home ዜና በትግራይ ወባ፣ ኮሌራ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ እንዲሁም አባ ሠንጋ የተባለው የከብቶች በሽታ...

በትግራይ ወባ፣ ኮሌራ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ እንዲሁም አባ ሠንጋ የተባለው የከብቶች በሽታ በወረርሽኝ መልክ መከሰታቸው የትግራይ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

1008

—-

በእነዚህ በሽታዎች ምክንያት በርካታ ወገኖች ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን እና የሞት መጠኑ እየጨመረ እንዳለ ቢቢሲ ዘግቧል።

በትግራይ ወባ፣ ኮሌራ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ እንዲሁም አባ ሠንጋ የተባለው የከብቶች በሽታ በወረርሽኝ መልክ መከሰታቸው ቢቢሲ የትግራይ ጤና ቢሮ መረጃ ጠቅሶ  ዘግቧል።

ከእነዚህ በሽታዎች መካከል ውስጥ ሶስቱ በከፍተኛ ደረጃ ስጋት መሆናቸው ያስታወቀው የትግራይ ጤና ቢሮ የእብድ ውሻ በሽታ፣ አባ ሠንጋ እንዲሁም ወባ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረ የመድሃኒት እጥረት፣ የጤና ተቋማት መውደም እንዲሁም የመገናኛ መንገዶች መቋረጥና የአቅርቦት እጥረት ከተያያዥ ችግሮች ጋር ተደማምረው ለበሽታዎቹ መስፋፋት ዋና ምክንያቶች ሆነዋል።

ከወረርሽኞቹ መካከል አባ ሠንጋ የተባለው ከከብቶች ወደ ሰው የሚተላለፈው በሽታ በትግራይ ማእከላዊ ዞን ናዕዴር ዓዴት ወረዳ ውስጥ 10 ሰዎች መያዛቸውን የቢሮው መረጃ ያመለክታል።

ይሁን እና ከየወረዳዎቹ ወደ ትግራይ ጤና ቢሮ የሚመጡ ሪፖርቶች እንደሚያመላክቱት ግን በበሽታው የተጠቁ በርካታ ሰዎች መኖራቸው እንሚያመላክት ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያስረዳው።

እስካሁንም ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባካሄደው ጥናት ከእንስሳት ጋር ንክኪ ከነበራቸውና ስጋ ከበሉ 120 ሰዎች መካከል 34 በበሽታው እንደተያዙ እና ሁለት ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ አረጋግጧል።

ሌላው የጤና ስጋት የሆነው የእብድ ውሻ በሽታም በ11 የትግራይ ወረዳዎች 41 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

እንዲሁም በበሽታው የታመሙ ሰዎች ለማከም የሚረዳ መድሃኒት ባለመኖሩ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቤታቸው በባህላዊ መንገድ አልያም ወደ ባህላዊ ሐኪም በመሄድ መፍትሔ ለማግኘት እንዲጥሩ እያስገደዳቸው ነው ሲል BBC ዘግቧል።

በትግራይ ከፍተኛ የጤና ስጋት የፈጠረው የወባ ወረርሽኝም በጦርነቱ ሳቢያ ተገቢ የህክምና አገልግሎት፣ የህክምና አቅርቦቶች እና መደበኛ ክትትል ባለመኖሩ የበሽታው መስፋፋትና በበሽታው ምክንያት የሚያጋጥም ሞት እየተመዘገበ መሆኑ የትግራይ ጤና  ቢሮ ለቢቢሲ ገልጿል።

በትግራይ የመገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት በመቋረጡ እና ከየአካባቢው የሚቀርቡ መረጃዎች ያልተሟሉ በመሆናቸው የበሽታው መስፋፋት በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት እንዳዳገተው ገልጿል።

ወባ ከሰኔ 2020 ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ በወረርሽኝ መልክ እየተዛመተ መሆኑን የትግራይ ጤና ቢሮ አስረድቷል።

በትግራይ ውስጥ ከ10 በላይ ወረዳዎች የወባ በሽታ መስፋፋት ታይቷል ያለው ሪፖርቱ በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀረ ወባ መድሐኒት እና ሌሎች የህክምና አቅርቦቶች ባለመኖሩም ሁኔታው ተባብሷል ብሏል።

ወረርሽኙን በጊዜ መቆጣጠር ካልተቻለ ወደ ብዙ የትግራይ አካባቢዎች ሊዛመት እንደሚችል ነው የትግራይ ጤና ቢሮ ያስጠነቀቀው ሲል BBC ዘግቧል።

ሄለን ወ/ዮሀንስ