Home Uncategorized በአዲስ አበባ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እስርና ሰቆቃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የግፉ ሰለባዎች ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እስርና ሰቆቃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የግፉ ሰለባዎች ተናገሩ፡፡

626

——

በሀገሪቱ ሰላም ማስፈን የተሳነው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ትግራዋይን በግፍ ማሰር፣ ማሰቃየት እና ከስራ ማባረር ስራዬ ብሎ እንደተያያዘውም ነው የትግራይ ተወላጆች የገለጹት፡፡

የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ገብሮ ላለፉት 27 አመታት በደሙ ያነፃትን አዲስ አበባ አሁን ላይ ለትግራይ ተወላጆች የምድር ሲኦል ሁናባቸዋለች፡፡ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የሀገሪቱን ሰላም ማስፈን ሲሳነው ሁሉም ወንጀሎች ትግራዋይ ላይ በማላከክ በአዲስ አበባ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የሚፈጽመውን የጅምላ እስርና ስቃይ አጠናክሮ መቀጠሉን ነው የግፉ ሰለባዎች የሚገልጹት፡፡

በአዲስ አበባ በየመንገዱ እየታፈሱ ከሚታጎሩ የትግራይ ተወላጆች በተጨማሪ መሰረተ ቢስ በሆኑ ውንጀላዎችም ለእስር ተዳረጎው እየተሰቃዩ እንዳሉም የተጎጂ ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡

የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ያለው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በአዲስ አበባ በሚኖሩ የትግራይ ተወላችም ከስራ ገበታቸው በማባረርና ንብረታቸውን በመዝረፍ እንዲራቡ እያደረገ ነው ብለዋል የግፉ ሰለባዎች፤ እነዚህ ሰለማውያን የትግራይ ተወላጆች እየተለቀሙ እንዲታሰሩና ከስራ ገበታው እንዲባረሩ እየተደረገ ነው ይላሉ፡፡

በጅምላ የታሰሩ የትግራይ ተወላጆች ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው በመሆኑ  የአለም ማህበረ-ሰብና የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ አካላት በትግራይ ተወላጆች እየደረሰ ያለውን ስቃይና ሰቆቆ እንዲያስቆሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በተጨማሪ በአፋር፣ በአማራና በሌሎች የአገሪቱ አካካቢዎች  የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን ማንነትን መሰረት ያደረገ ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በይብራህ እምባየ