Home ዜና በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንደአዲስ ባገረሸው እስራትና አፈሳ ሰለባ እየሆኑ እንደሆኑ...

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንደአዲስ ባገረሸው እስራትና አፈሳ ሰለባ እየሆኑ እንደሆኑ ተገለፀ፡፡

1122

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያነጣጠረ እስራትና እንግልት ድጋሚ በፋሸስቱ የአብይ ቡድን እየታፈሱ የፖሊሶችና የጠበቃዎች  ኪስ ሞምያ እየሆኑ እንዳለ ከቦታዉ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት በየማጎሪያ ቤቱና ከስራ ዉጭ ሆነዉ እየተሰቃዩ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች አሁንም ባልፈፀሙት ወንጀል እየታፈሱ እየታሰሩ እንዳሉና ለዋስ ክፈሉ እየተባሉ  ለብዝበዛ እየተዳረጉ እንደሆነ  ምንጮች አስታዉቀዋል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ትግራይና ትግራዋይን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት  ታሪክ ይቅር የማይለዉ ግፍ እየፈፀመና እስራትም   አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፋሽስቱ ቡድን ለበርካታ ዓመታት  በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጁንታዉን እያገዛቹሁ ነዉ  በማለት ትግራዋይን ባገኙበት እያፈሱ በማሰር ለዋስ ከአቅማቸዉ በላይ  የሆነ ገንዘብ እንዲከፍሉ እያደረጋቸው እንደሆነ ታዉቋል፡፡

እነዛ በየቀኑ ትግራዋይን በማሰር ገንዘብ በመሰብሰብ ኪሳቸዉ ያበጠዉ የአዲስ አበባ ፖሊሶችና ጠበቆች የትግራይ ተወላጆችን በማሰር ጉቦ  እንዲከፍሉ በመመሳጠር ለፖሊስና ለዳኞች ጨምሮ ለዋስ  በሚል ተልካሻ ምክንያት  ከአቅማቸዉ በላይ የሚጠየቁት ገንዘብ ለብድርና ለብዝበዛ እየተዳረጉ እነደሆነ ተገልጧል፡፡

በጎዳናዎች ሻይ ቡና የሚሸጡና በቀን ስራ በምስራት የሚተዳደሩ የአዲስ አበባ ነዋሪ የትግራይ ተወላጆች ምንም ወንጀል ሳይፈፅሙ በማንነታቸዉ ብቻ ያለ አግባብ እየታፈሱ ከጁንታዉ ጋር ግንኙነት አላቹ፤ ገንዘብ ትልካላቹ  የሚል ጥቆማ ደርሶናል በሚል ተልካሻ ምክንያቶች የፖሊስና የዳኞች ኪስ መሙያ  መሆናቸዉ የግፉ ሰላባ ከሆኑት በአንደበታቸዉ  የተናገሩት  መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሞባይላቸዉ እየተፈተሸ  የትግራይ ባንዲራና የታጋዮች ምስል ይዘህ ተገኝለተሃል፣ በትግል ዘፈን ቤት በመዝጋት እየጨፈራቹሁ ነዉ በሚል ተልካሻ ምክንያት በማቅረብ የትግራይ ተወላጆች በካባድ ስቃይ ዉስጥ እንደሚገኙና አፈሳዉ ተጠናክሮ እንደቀጠለ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ትግራዋይን በማሰር አዲስ የቢዝነስ ስራ እየሆነ መምጣቱ የሚናገሩት ሰለባዎቹ   አቃቂ ቃሊቲ በሚባል አካባቢ በሚገኘዉ የደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት ውስጥ  ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች አንድ ላይ መታሰራቸው  ምግብም ሆነ ልብስ ማስገባት እንደማይችሉም ተናግረዋል፡፡

ከታሰሩት ዉስጥ  ከሳውዲ ዓረቢያ  ተመላሾች  እንደሚገኙበትና ገንዘብ ስለሌላቸዉ አንድላይ በተኙበት ታፍሰዉ የተወሰዱና  እነዚህ ሰዎች ማንም ሰዉ ሊጠይቃቸዉም ሆነ ምግብ ሊያቀብሏቻዉ በመከልከላቸዉ ወደ አዋሽ ሊወስደዋቸዉ እንደሚችሉ ስጋታቸዉን በመግለፅ ሁሉም ትግራዋይ ድምፅ እንዲሆናቸዉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፋሽስቱ ቡድን ከዚህ በፊትም በአዲስ አበባ ተወልደዉ አድገዉ ትግራይን በዉል የማያዉቁትን ጭምር መታወቂያቸዉ እየታየ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸዉ የሚገልፅ ስም ካለዉ እየተለየ ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመባቸዉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ