Home ዜና ተስፋፊው የአማራ ፋኖ በምስራቅ ሀረርጌ ጉርሱም ወረዳ አራት ሰዎችን አሳፍራ ወደ አዳማ...

ተስፋፊው የአማራ ፋኖ በምስራቅ ሀረርጌ ጉርሱም ወረዳ አራት ሰዎችን አሳፍራ ወደ አዳማ ታመራ የነበረች አምቡላንስን ማጋየቱ ተነገረ፡፡

1691

Addis standard የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮን ጠቅሶ እንደዘገበው  አክራሪውና ተስፋፊው ፋኖ የፈጸመው ጥቃት በቦሰት ወረዳ ቃዋ በምትባል የገጠር ቀበሌ ነው፡፡

ቢሮው በፌስቡክ ገፁ እንዳስነበበው ይህ የፋኖ አክራሪ ሃይል በየጊዜው በአካባቢው የሚደርሰውን ግድያና ዝርፊያ ተጠያቂ ነው፡፡ የዚሁ አክራሪና ተስፋፊ ፋኖ ተግባር በአካባቢው ለሰላምና መረጋጋት ጠንቅ እየሆነ መምጣቱ የ Addis standard ዘገባ ያመለክታል፡፡

ከቅርብ ቀናት በፊት በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአክራረውና ተስፋፊው ፋኖ በደረሰ ጥቃት 26 ሰዎች መገደላቸውን Addis standard በዘገባው አስታውሷል፡፡

አክራሪውና ተስፋፊው ፋኖ  በተመሳሳይ ከቅርብ  ቀናት በፊት ወደ አፋር ያመሩ የነበሩ ሰባት ማእድን የጫኑ የትላልቅ የጭነት ተሸከርካሪዎችን ማገቱን ዘገባው ጨምሮ አስረድቷል፡፡