Home Uncategorized አምባገነኑ ኢሳያስ  ትግራዋይ ከትምህረት እንዲርቅ  በማድረግ ትግራይ ያልተማረ ትዉልድ እንዲኖራት  የቻለውን አድርጓል፡፡

አምባገነኑ ኢሳያስ  ትግራዋይ ከትምህረት እንዲርቅ  በማድረግ ትግራይ ያልተማረ ትዉልድ እንዲኖራት  የቻለውን አድርጓል፡፡

1190

ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ጥራት ያለዉ ትምህረት በሰፊዉ እንዲዳረሰ የሚያሰችል መጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንት በማካሄደ ፣የትምህርት እድል፣ የተማረ በመልካመ ስነ ምግባርና ስነ ዜጋ እሴቶች የታነፀ ወጣት ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡፣

 መብትና ግዴታዉን ያወቀ ህብረተሰብን ለመገንባት የሚያስችል ፣ህፃናት ወደ ትምህረት ቤት እንዲመጡ፣ትምህረትና እዉቀትን ለሰዉ ልጅ እኩል እንዲዳረሰ  በኢትዮጰያ ፣የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ብቻ ሳይሆን  የሙያና የቴክኒከ ከዚያም አልፎ የከፍተኛ ተቋማት በከፍተኛ ደረጃ እንዲስፋፉ ወቅት ነበር ፡፡ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት  ከትምህርት ጋረ ተያየዞ የመጣዉ ለዉጥ በግንቦት ሃያ ከተገኙት ትሩፋቶች ዉስጥ አንዱ እንደሆነ የትግራይ መምህራን ይናገራሉ፡፡

ይሁንና  ስልጣን ላይ የተቆናጠጠዉ ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና  ግብረ አበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀሙት ባለዉ ጀኖሳይድ የትግራይን ህዝብ ለማዳከም  ለረጅም ግዜ አቅደዉ  በትኩረት ከተንቀሳቀሱባቸዉ መካከል  አንዱ የትምህረት ዘርፍን ማውደም  በመሆኑ   ትግራይንና ህዝቧ ወደ ሃላ ለመመለሰና ተተኪ ትዉለድ  አንዳይፈጠረ ታልሞ የተሰራ ድርጊት ነዉ ብለዋል ፡፡

የትግራይ ህዝብን እንደህዝብ ከምድረ ገፅ  ለማጥፋት የነበረዉ ፍላጎት ያልተሳካለት አምባገነኑ ኢሳያስ ዜጎቹን እዉቀትን እንዲቀስሙ ከማስተማረ  ይልቀ የስደት መንገድን  በማስተማሩ ምክንያት የትግራይ ትዉልድ ከትምህረት እንዲርቅ  ትግራይ ያልተማረ ትዉልድ እንዲኖራት  አድርጓል  ብለዋል ፡፡

መምህራኑ አክለዉም ትምህርት ትዉልድ የምታንፅበትና  እዉቀት የምታገኝበት በመሆኑ  የኢትዮጰያ መምህራን ማህበር   ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሲያወድም፡ በትግራይ በተፈጠረዉ ከበባና ክልከላ ምክንያት የትግራይ መምህራን በርሃብና በመድሃኒት እጦት ሂወታቸዉን እያጡ ባሉበት ወቅት  ዝምታን መምረጡ የሚያሳዝን ድርጊት ነዉ ብለዋል፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ