Home ዜና አምባገነኑ ኢሳያስ ኢትዮዽያን መዳፉ ውስጥ ለማስገባት አምሳያውን ስርዓት ለመትከል ሲታትር እንደነበረ ኤርትራዊ...

አምባገነኑ ኢሳያስ ኢትዮዽያን መዳፉ ውስጥ ለማስገባት አምሳያውን ስርዓት ለመትከል ሲታትር እንደነበረ ኤርትራዊ ታጋይ አጋለጠ፡፡

979
0

የዛሬ  አያድርገውና  ኤርትራ እንደ ሀገረ እንድትፈጠር በለጋ ዕድሜያቸው ከታገሉ  የኤርትራ ህዝብን  ከባርነት  እና ከጭቆና ቀምበር ያለቀቁ እንቁ ታጋዮች መካከል አንዱ ናቸው:: ኤርትራዊ ነባር ታጋይ በያን ሐዱሽ

እንደ ወጣትነት ራእያቸው ሳይሆን ቀርቶ ኤርትራም 50 ዓመታትን በተስፋ የጠበቀችው ነጻነት እንደ ጉም በኖ የኤርትራ ህዝብ ከጎረቤቶቹ ጋር በሰላም ከማደግ ይልቅ ደም ያቃባውን አምባገነን እጅ ውስጥ ወደቀች::

ሰው በላው የአምባገነኑ ኢሳያስ  ስርዓት  የነጻነት ታጋዮችን መረሸን፣ ማሰቃየት፣ ወደ ዘብጥያ አውርዶ ደብዛቸው ማጥፋት የተለመደ ተግባር ነው፤ ታሪካቸውን ያወጉን ነባር ታጋይ  በያን ሐዱሽም እጣ ፈንታቸው ከዚህ የተለየ አልነበረም::

ነገሩ እንዲህ ነው በኢትዮዽያ ተወረረርኩ ሲል ዓለምን ለማወናበድ የሰራው ሸፍጥ ተጋልጦ በ ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሽንፈትን ተከናንቦ እርቃኑ የቀረው የአምባገነኑ #ኢሳያስ ስርዓት  ኢትዮዽያን እና የምስራቅ #አፍሪካ ቀጠናን ለማተራምስ ያለውን ህልም ለማሳካት የዓመታት ወታደራዊ ልምድን ያካበቱ ነባር ታጋዮች እና የትግል ጓዶቹን  በክህደት ከተሸጡት መካከል ነባር ታጋይ በያን ሐዱሽ  አንዱ እንደነበሩ ይናገራሉ::

ለሁለት አስርት ዓመታት ገደማ በጦርነት ስትታመስ ቆይታ ገና ለገና ህዝባዊ ስርዓተ መንግስት ተክላ ልማት፣ ሰላም እና ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ ወዲህ ወዲያ ሰትል በነበረቸው #ኢትዮዽያ ላይ ዓይኑን የጣለው አምባገነኑ ኢሳያስ ኢትዮዽያም ሆነ ቀጠናውን ለማተራመስ አሸባሪው የአልሸባብ ቡድንን ጨምሮ በኢትዮዽያ ነውጥ ናፋቂ ሀይሎችም ያሰለጥን ነበር  እና ከዛን ግዜ ጀምሮ በጠነሰሰው ሴራ ኢትዮዽያ ውስጥ እርሱን የሚመስል ስርዓት ለመትከል ሲታትር እንደነበር ነባር ታጋዩ ይናገራሉ::

ነባር ታጋይ በያን ሐዱሽ   ከ30 ዓመታት በፊት በዚሁ ሳምንት የነጻነት ዜና እና  ተስፋ ዘንቦባት በነበርችው ኤርትራ መኖር ቢሹም  ያ ሳይሆን ቀርቶ ሞትን ሸሽተው በረሀውን አቆራርጠው የስደት ኑሮ እየገፉ ካሉ ኤርትራውያን መካከል አንዱ ናቸው::

የአምባገነኑ ኢሳያስ  ስርዓት በስመ ወታደራዊ አግልግሎት ወጣቶችን  በተለያዩ ሀገራት ልኰ በጦርነት ማስጨረሱን ሳይበቃ ዛሬም በቴክኖለጂ የት እና የት በደረሱ ሀገራት #ሩስያ እና #ዩክሬን መካከል በሚደረገው ጦርነት ከሩስያ ጎን መሰለፉ የኤርትራ ወጣቶችን ከመሽጥ ወደኋላ የማይልበት ምክንያት የለም ብለዋል::

Previous articleኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን የሚያጎለብት አካታችና ሁሉን አቀፍ የሆነ ውይይት ያሰፋጋል ተባለ፡፡
Next articleየትግራይ አርሶ አደር በመጪው የክረምት ወራት የእርሻ ምርት ማምረት ካልቻለ በቀጣዩ ዓመት የከፋ የርሃብ አደጋ   ተዘገበ፡፡