Home ዜና ኢትዮጵያን እንደ ሶርያ

ኢትዮጵያን እንደ ሶርያ

1126

የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች ግዛትን የማስፋፋት ፍላጎትና በግፋ በለው ፖለቲካ ምክንያት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች አብሮነትና አንድነት አደጋ ውስጥ ከተውታልቷል፡፡

የአማራ ልሂቃንን ፍላጎት ለማሳካት ትግራዋይን ማጥፋት የሚል የተሳሳተ ስሌት ይዞ የመጣው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን አሁን ላይ ኢትዮጵያ ከትግራይ እስከ ኦሮምያ፣ ከዓፋር እስከ ቤንሻንጉል፣ ከሲዳማ እስከ ጅንካ በአብዛኛው የአገሪቱ አከባቢዎች ግጭት፣ ሁከት የዕለት ተዕለት የዜና አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ይፋዊ ጀኖሳይድ ጦርነት ከማወጁ በፊት ትግራይ ላይ የሚለኮሰው ጦርነት መላ አገሪቷን እና ምስራቅ አፍሪካን የሚያተራምስ እንደሆነ ታጋይ አቶ ስዬ አብርሃ በአንድ ወቅት  እንዲህ ብለው ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግር ይፈታልን፤  የልማት  ጥያቄ ይመለስልን በማለት ከአራት አመት በፊት የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ መደመር በሚል የማደናገሪያ እሳቤ የህዝብን ጥያቄ ሳይመልስ  ስልጣን ላይ ለመቆናጠጥ የበቃው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን፤ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ስለ ዲሞክራሲና ስለ ልማት ጥያቄ ማንሳት ይቅርና አገሪቱ ሰላምና መረጋጋት የራቀባት አገር ሆናለች፡፡

 የዚህ ዋነኛ ጠንሳሽ ደግሞ በግዛት ማስፋፋት ፍላጎት የተጠናወተውና የግፋ በለው ፖለቲካ እያራመደ ያለው የአማራ ተስፋፊ ሀይል ነው፡፡ አዲስ አበባ፣ ወልቃይት፣ ራያ፣ መተከልና አሳይታ በችሮታ ካልተሰጠን ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያ እናደርጋታለን በማለት በኢትዮጵያውነት  ካባ ስም ሲያራምደው ከነበረውን የሃሰት ትርክት ወጥቶ የአማራ የግዛት መጠቅለል እቅድ ካልተሳካ ኢትዮጵያ ብትንትንዋ ትውጣ እያለ ነው፡፡

ይሄ ሀይል አዲስ አበባ፣ ወልቃይትና ራያን ከመመኘቱ በፊት  አማራ የሚለው ስያሜና ማንነትን የማረጋገጥ መብት  በትግራይ ህዝብ መስዋእትነት የመጣ  ለመሆኑ የዘነጋው ይመስላል፡፡

የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች በግዛት ማስፋፋት ፍላጎት የኢትዮጵያን አንድነትና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አብሮነትን እያናጉት እንደሆነ የፋሽስቱ አብይ  ቅጥረኛ ሽመልስ አብዲሳም ከኦሮ-ማራ የውሸት ጥምረት ወጥቶ ሀቁን መመስከር ጀምሯል፡፡

አብይ ሙስያችን፤ አሻጋሪያችን ብሎ ስሙን ሲያማካሹት የነበሩት የአማራ ልሂቃንም  አሁን ላይ ፋሽስቱ አብይ ለአለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ይቅረበልን ማለት ጀምረዋል፡፡

የአማራ ልሂቃንን ፍላጎት ለማሳካት ትግራዋይን ማጥፋት የሚል የተሳሳተ ስሌት ይዞ የመጣው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ለአለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት እስከሚቀርብ ድረስ ግን አገሪቷን ከመፍረስ መታደግ አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች  ትግላቸውን አጠናክረው የመቀጠሉ ጉዳይ ለነገ ሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡

ይብራህ እምባየ