Home ዜና ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን የሚያጎለብት አካታችና ሁሉን አቀፍ የሆነ ውይይት...

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን የሚያጎለብት አካታችና ሁሉን አቀፍ የሆነ ውይይት ያሰፋጋል ተባለ፡፡

2667

ችግሮችን በንግግርና በውይይት ከመፍታት ይልቅ ጉልበትን የመፍትሄ አማራጭ ተደርጉ መወሰዱ ሃገሪቱ ለገባችበት ሁለንተናዊ ቀውስ ቀዳሚው ምክንያት ነው ብለዋል ምሁራኑ፡፡

ጨቋኙና አምባገነኑ የደርግ አገዛዝ ተገርስሶ ኢህአዴግ በትረ ስልጣኑን ተረክቦ ኢትዮጵያን በመራባቸው 27 አመታት በሀገሪቱ ህብረ-ብሄራዊ አንድነት ተረጋግጦ ዜጎች በቋንቋቸው እንዲማሩ ብሎም ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ያስቻለ የፌደራሊዝም ስርዓቱ መልካም ውጤቶች የታዩበት ግዜ እንደነበር ብዙዎች ይመሰክራሉ::

በዚሁ ሂደት ዋነኛ ተዋናይ እና መሰረት የሆነው የትግራይ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ የቋንቋ߹ የብሄር፣ የሀይማኖት ብዝሃነት በስርአት አቻችሎ በመሄድ ችግሮቹን በውይይት በመፍታት ረገድ አርአያ የሚባል እንደነበር የህግና የነገረመለኮት ምሁራን ይገልፃሉ፡፡

ይህ ሲሆን ግን በሀገሪቱ የመጣው ለውጥና እድገት ያልተዋጠላቸው ያለፈው ስርዓት ናፋቂዎች ከየአቅጣጫው ተሰባስበው የትግራይ ህዝብ ለዘመናት የገነባውን ባህሉን ቋንቋውን ሀይማኖቱን እሴቶቹንና ማህበራዊ መስተጋብሩን ለማጥፋት ጀኖሳይድ ጦርነት አውጀው ያልፈፀሙበት ግፍ የለም፡፡

ችግሮችን በንግግርና በውይይት የመፍታት ልምድ ባለፉት 27 አመታት ዳብሮና አመርቂ ውጤቶችም የተመዘገቡበት ነበር የሚሉት ምሁራኑ አሁን ላይ ያሁላ ጠፍቶ ጉልበት የመፍትሄ አማራጭ የሆነበት ጊዜ ደርሰናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ አግላይና ጨፍላቂ ከሆነ አስተሳሰብ በመውጣት ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን የሚያጎለብት አካታችና ሁሉን አቀፍ የሆነ ውይይት ሊደረግ ይገባል ሲሉ የህግና የነገረመለኮት ምሁራኑ ምክረሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

ዊንታ ዘላለም