Home Uncategorized እውነታን ያላገናዘበው የአሜሪካ ውሳኔ

እውነታን ያላገናዘበው የአሜሪካ ውሳኔ

364

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ዙርያ ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ከዚህ ቀደም ለሚታወቅበት አቋሙ የሚቃረን ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል፡፡ከሶስት ወራት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶንዮ ብሊንከን የፅሕፈት ቤታቸው ዓመታዊ ሪፖርትን አስመልክተው ይፋ ባደረጉት መግለጫ የጥፋት ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል፣ በሰብአዊነት የተፈፀመ ወንጀልና የዘር ማፅዳት ድርጊትን መፈፀማቸው በማስረጃ በማስደገፍ ማቅረባቸው የጠቀሰው ሂዩማን ራይትስ ዎች አሁን ወደ ኮንግረስ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ግን ለዚህ ማስረጃ የሚቃረንና እውነቱን ገደል የከተተ ነው በማለት ተቃውሞታል፡፡የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ማንነትነ መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ፣ በጅምላ የተፈፀመ ፆታዊ ጥቃትና ጭፍጨፋ መገለጫቸው የሆነው የጥፋት ሃይሎች በሶስት ወራት ውስጥ ተአምራዊ ለውጥ ማምጣት አይችሉም ያለው ሂዩማን ራይትስ ዎች የአሜሪካ የውሳኔ ሃሳብ ተጠያቂነት እንዳይረጋገጥ ዕንቅፋት መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ፆታዊ ጥቃትና ጭፍጨፋ የጥፋይ ሃይሎች መገለጫ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ መግለፃቸው ያስታወሰው ሂዩማን ራይትስ ዎች በትግራይ ያለው ሁኔታ አሁንመ አልተቀየረም ብሏል፡፡የአሜሪካ መንግስት ላለፉት 30 ዓመታት በሰብአዊ መብት ጥሰት ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ፍትሃዊና ዓለም ዓቀፍ ህግን የሚያስከብር እንደነበር ያወሳው ሂዩማን ራይትስ ዎች በቦስንያ ሄርዞ ጎቪንያ፣ በሩዋንዳ፣ ኢራቅ፣ ዳርፉር፣ ቻይናና ማይናማር ውጤታማ ውሳኔዎች አስተላልፏል ብሏል፡፡በሶሎሞን ኣስመላሽ